ፖለቲካ
ቻይና፤ አሜሪካ ወታደራዊ ስምሪት ስላጠናከረች ቀጠናው በተጠንቀቅ ላይ እንዲሆን አሳሰበች
ቻይና ያስጠነቀቀችው አሜሪካ በጃፖን ላይ አቶሚክ ቦንብ የወረወረችበትን አየርፊልድ ለማቋቋም ፍላጎት አላት የሚሉ ሪፖርቶች ከወጡ በኋላ ነው
የቻይና ጦር፣ አሜሪካ የምታደርገውን እንቅስቃሴ እንደሚቆጣጠር የመከላከያ ሚኒስቴሩ ገልዋል
ቻይና፤ አሜሪካ ወታደራዊ ስምሪት ስላጠናከረች ቀጠናው በተጠንቀቅ ላይ እንዲሆን አሳሰበች።
የቻይና መከላከያ ሚኒስቴር በትናንትናው እለት እንዳስታወቀው አሜሪካ በቀጣናው ወታደራዊ ስምሪት ስላጠናከረች እስያ-ፖሲፊክ በከፍተኛ ተጠንቀቅ ላይ እንዲሆን አሳስቧል።
ቻይና ያስጠነቀቀችው አሜሪካ በቀጣናው በጃፖን ላይ አቶሚክ ቦንብ የወረወረችበትን አየርፊልድ ለማቋቋም ፍላጎት አላት የሚሉ ሪፖርቶች ከወጡ በኋላ ነው።
የቻይና ጦር፣ አሜሪካ የምታደርገውን እንቅስቃሴ እንደምትቆጣጠር እና በቀጣናው የቻይናን የማሪታይም መብት፣ደህንነት እና ሉአላዊነት በጥብቅ እንደሚያስጠብቅ የመከላከያ ሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ዉ ኩያን ተናግረዋል።
በታህሳስ ወር መጀመሪያ የአሜሪካ የአየር ኃይል ጀነራል በደን የተወረረውን 'ቲኒያን ኖርዝ ኤየርፊልድ' አጽድታ ጥቅም ላይ እንደምታውለው ገልጸው ነበር።
አሜሪካ ከዚህ ኤየርፊልድ በመነሳት በኢንዶፖሲፊክ ቀጣና ጀቶቿን ለማሰማራት ይረዳታል ተብሏል።
የአሜሪካ ግዛት በሆነችው በማሪያና ደሴት የሚገኘው ቲኒያን ኤየርፊልዱ ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በኋላ ተትቶ ነበር።