674ኛ ቀኑን በያዘው የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ምን አዳዲስ ክስተቶች ተስተናግደቀዋል?
ሩሲያ በሁለት በዩክሬን ሰሜን ምስራቅ በሚገኙ ከተሞች ላይ የአየር ድብደባ መፈጸሟን የከተሞቹ ከንቲባዎች አስታውቀዋል።
ሩሲያ የአየር ድብደባውን በዩክሬን ሰሜን ምስራቅ በሚገኙ ክሃርኪቭ እና ለቪቭ የተባሉ ከተሞች መፈጸመዋ ነው የተነገረው።
የክሃርኪቭ ከተማ ከንቲባ እንዳስታወቁት ሌሊቱን በከተማዋ ላይ ከፍተኛ የሆነ በርካታ የሚሳዔል ድብደባ ተፈጽሟል፤ የለቪቭ ከተማ ከንቲባ በበኩላቸው ሁለት የሚሳዔል ጥቃቶች መፈጸማቸውን አስታውቀዋል።
በሁለቱ ከተሞች የሚሳዔል ጥቃት መፈጸሙ ቢነገርምን በሰው ላይ ጉዳት ስለመድረሱ እስካሁን የወጣ ሪፖርት የለም።
የክሃርኪቭ ቀጠናዊ መታደራዊ አመራር እንደስተወቁት ሩሲያ በከተማዋ ላይ አስር የሚደርሱ የድሮን ጥቃቶችን ፈጽማለች።
ከአየር ድብደባዎቹ በተጨማሪም በኦዴሳ ከተማ ላይ ሩሲያ የድሮን ጥቃት ማድረሷን መረጃዎች ጠቁመዋል።
በኦዴሳ የድሮን ጥቃቶችን ተከትሎም በከተማዋ በሚገኙ ግዙፍ ህንጻች ላይ የእሳት አደጋዎች ተቀስቅሰው እንደነበረም የአካባቢው አስተዳዳሪዎች አስታውቀዋል።
የዬክሬን አየር ኃል ከሩሲያ ከተላኩ ስምንት ድሮኖች ውስጥ ሰባት ድሮኖችን የሀገሪቱ የአየር መከላከያ ስርዓት መትቶ መጣሉን አሰታውቋል።
ሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ በክሬሚያ ላይ ሊፈጸም የነበረ የድሮን ጥቃቶችን ማክሸፉን አስታውቋል።