አዲሱ የአርቲፊሺያል ኢንተለጀንስ መተግበሪያ ባይዱ በተሰኘው የቻይና ኩባንያ መሰራቱ ተገልጿል
ቻይና የአሜሪካውን ቻትጂፒትን ለመገዳደር "ኢርኒ ቦት" የተሰኘ ፈጠራ ይፋ አደረገች።
የአሜሪካው ኦፕን ኩባንያ ቻትጅፕቲ የተሰኘ የአርትፊሺያል ኢንተለጀንስ መተግበሪያ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
ይህ መተግበሪያ ለህዝብ ይፋ ከተደረገ በኋላ በአንድ ሳምንት ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደንበኞችን ማፍራት ችሎ ነበር።
አሁን ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ብዙ ተጠቃሚ ያለው ጎግል ኩባንያን በአጭር ጊዜ ውስጥ ከውድድር ሊያስወጣው ይችላል የተባለው ይህ መተግበሪያ እንደ ቻይና ባሉ ሀገራት እንዳይሰራ ታግዷል።
ቻይና አሁን ላይ ኢርኒ ቦት የተሰኘ የአርቲፊሺያል ኢንተለጀንስ መተግበሪያ ይፋ ማድረጓን ሮይተርስ ዘግቧል።
የአሜሪካውን ቻትጅፒቲ መተግበሪያን ለመፎባከር ተብሎ የተሰራው ይህ ኢርኒ ቦት በባይዱ የቴክኖሎጂ ኩባንያ መሰራቱ ተገልጿል።
ባይዱ ኩባንያ ይህን መተግበሪያ ከአራት ዓመት በፊት ጀምሮ ሲያለማው እንደቆየ እና ሶስት ቢሊዮን ዶላር እንዳስወጣው የኩባንያው ስራ አስኪያጅ ሮቢን ሊ ተናግረዋል ።
ይሁንና ይህ ቻይና ሰራሽ መተግበሪያ በቻይናዊያን ባለሀብቶች እንዳልተወደደ ተገልጿል።
መተግበሪያው ልክ እንደ አሜሪካው ቻትጅፒቲ ቴክኖሎጂ በራሱ የምስል፣ ድምጽ እና የጽሁፍ ይዘቶችን ማከናወን አለመቻሉ ላለመወደዱ ዋነኛ ምክንያት ነው ተብሏል።
በርኒ ቦት የጽሁፍ መልዕክቶችን፣ ምስል እና ሌሎች ይዘቶችን በቀረበለት መረጃ መሰረት ለኩባንያዎች በራሱ ማዘጋጀት ይችላል የተባለ ሲሆን በተወሰነ መልኩ ገደብ እንደተጣለበት በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።
በርኒ ቦት በተለይም አንድ አይነት እና አስቀድሞ በተሰጠው መረጃ እና ኢንፎርሜሽን መሰረት ለኩባንያዎች አገልግሎት ይሰጣል የተባለ ሲሆን በራሱ እና በሰዎች ፍላጎት መሰረት አገልግሎት መስጠት አይሰጥም።
ባይዱ ኩባንያ አዲሱን መተግበሪያ ይፋ ባደረገ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ከ650 በላይ ኩባንያዎች አብረው ለመስራት ጥያቄ እንዳቀረቡም ተገልጿል።