ቻይና እና አሜሪካ በዓለም የንግድ ድርጅት ስብሰባ ላይ ከባድ የቃላት ልውውጥ ማድረጋቸው ተገለጸ
ቤጂንግ ዋሽንግተንን “ጉልበተኛ” ስትል አሜሪካ ደግሞ ተቀናቃኞቿን "ህገ-ወጥ" በማለት ወንጅላታለች
ዋሽንግተን የዓለም የንግድ ድርጅት አለመግባባት የሚፈታበትን ስርዓት ወቅሳለች
ቻይና እና አሜሪካ በዓለም የንግድ ድርጅት ስብሰባ ላይ ከባድ የቃላት ልውውጥ ማድረጋቸው ተገለጸ
ቻይናና አሜሪካ አርብ ዕለት በተካሄደው የዓለም ንግድ ድርጅት ስብሰባ ላይ የሰላ ትችት ተለዋውጠዋል።
ቤጂንግ ዋሽንግተንን “ጉልበተኛ” ስትል አሜሪካ ደግሞ ተቀናቃኞቿን "ህገ-ወጥ የበቀል እርምጃ" በመውሰድ ወንጅላታለች።
የዓለም የንግድ ድርጅት የቻይና አምባሳደር ሊ ቼንግጋንግ በንግድ አለመግባባት ዙሪያ ንግግር አድርገዋል።
ዋሽንግተን በቻይና፣ ቱርክ፣ ኖርዌይ እና ስዊዘርላንድ ላይ በተላለፉት ተከታታይ የዓለም ንግድ ድርጅት ውሳኔዎች ላይ ይግባኝ ካቀረበች በኋላ፤ በንግድ አለመግባባቶች ዙሪያ አምባሳደሩ ተናግረዋል።
ሮይተርስ አገኘሁት ያለው የንግግሩ ግልባጭ "የአሜሪካ ባህሪ የሀገሪቱን ምስል የአንድ ወገን ጉልበተኛ፣ ደንብ ተላላፊ እና የአቅርቦት ሰንሰለት አደናቃፊ አድርጎ በግልጽ አሳይቷል" ብለዋል።
ከቻይና ጋር የብረት ንግድና ከሆንግ ኮንግ ጋር የነበረን ክርክርን ጨምሮ ድርጅቱ በቅርብ ሳምንታት ዩናይትድ ስቴትስ ላይ ውሳኔ ሰጥቷል። በውሳኔ ያልተደሰተችው ዋሽንግተንም ይግባኝ ብላለች።
የዓለም የንግድ ድርጅትን የአለመግባባት ስርዓትን ስትወቅስ የቆየችው ዋሽንግተን የተላለፈባትን ውሳኔዎች ነቅፋለች።
አሜሪካ ከቻይና ጋር ያላት የብረታ ብረት ታሪፍ ውዝግብ በስብሰባው ላይ አጀንዳ መሆኑ እንዳሳዘናት ገልጻለች።
አሜሪካ ወደ ውጭ በምትልካቸው ምርቶች ላይ ቤጂንግ "ህገወጥ የአንድ ወገን የበቀል እርምጃ" እየወሰደች ነው ስትልም ከሳለች።