ታይዋን በተዋጊ ድሮኖች ተከብቢያለሁ አለች
ታይዋንን እንደራሷ ግዛት የምታያት ቻይና ባለፉት ሶስት አመታት በደሴቷ ዙሪያ የምታደርገውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ጨምራለች
የቻይና አየር ኃይል ኑክሌር መሸከም በሚችለው ኤች-6 ታይዋን በመክበብ እንቅስቃሴ አድርጓል
በቻይና ሚዲያዎች ከፍተኛ ክብደት መሸከም ይችላል የሚባለው አዲሱ የቻይና ተዋጊ ድሮን ታይዋንን እየዞረ መሆኑን የታይዋን መከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል።
ታይዋንን እንደራሷ ግዛት የምታያት ቻይና ባለፉት ሶስት አመታት በደሴቷ ዙሪያ የምታደርገውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ጨምራለች።
ይህ የቻይና ተግባር ታይዋን በጫና ውስጥ ሆና የቻይናን ሉአላዊነት እንድትቀበል ለማድረግ ነው።
የታይዋን ፕሬዝዳንት ጻይ ኢንግ ዌን ከአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ኬቨን ማካርቲ ጋር ከተገናኙ በኋላ ቻይና በታይዋን ዙሪያ የጦርነት ልምምዶችን አካሂዳለች።
የታይዋን መከላከያ ሚኒስቴር ካለፉት 24 ሰአታት ወዲህ 19 የሚሆኑ የቻይና ወታደራዊ አውሮፕላኖች በደሴቲቱ የአየር መከላከያ ቀጠና ገብተዋል ብሏል።
ሚኒስቴሩ እንደገለጸው ባለሁለት ጭራ እየተባለ የሚጠራው የቻይና ድሮን ታይዋንን ከፊሊፕንስ የሚለየውን የባሽ መስመር ካቋረጠ በኋላ ወደ ምስራቅ ታይዋን አቅጣጫ በሯል።
ድሮኑ በመጨረሻም ወደ ቻይና ድንበር መመለሱን ሚኒስቴሩ ጠቅሷል።
የቻይና አየር ኑክሌር መሸከም በሚችለው ኤች-6 ታይዋን በመክበብ እንቅስቃሴ አድርጓል።
ምንም አይነት ተኩስ አለመተኮሱን እና የቻይና አየር ኃይልም የታይዋንን አየር ኃይል አልጣሰም ተብሏል።
ምንም አይነት ጥይት አልተተኮሰም እና የቻይና አውሮፕላኖችም የታይዋንን አየር ክልል አላቋረጡም ተብሏል።
የቻይና ወታደራዊ አውሮፕላኖች ከባለፈው አመት ጀምሮ እንደወሰን የሚቆጠረውን የታይዋን ባህርን መካከለኛ መስመር በተደጋጋሚ በማቋረጥ ላይ ናቸው።
የታይዋን መንግስት የቻይናን የሉዓላዊነት ጥያቄ ውድቅ በማድረግ የወደፊት እጣ ፈንታቸውን መወሰን የሚችሉት የደሴቲቱ ህዝብ ብቻ ነው ብሏል።