ቻይና ከህንድ ጋር ሰላማዊ ግንኙነት እንደምትፈልግ ስትገልጽ፤ ህንድ ግን መጀመሪያ የድንበሩ ውጥረት ይርገብ እያለች ነው
የቻይና እና ሕንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሕንድ መክረዋል
በፈረንጆቹ ሰኔ 2020 በተደረገው የእጅ ለእጅ ጦርነት 20 የህንድ እና አራት የቻይና ወታደሮች በሰሜን ሂማሊያን ግዛት ተገድለዋል
ሕንድ፣ በሕንድና በቻይና መካከል ባለው አወዛጋቢ ድንበር ላይ የሰፈሩ የሁለቱ ሀገራት ወታደሮች ከልተመለሱ ከቻይና ጋር ያላት ግንኙነት ሰላማዊ እንዳማይሆን ገልጻለች፡፡
የቻይና የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባለፈው አርብ በሕንድ ኒው ደልሂ ተገናኝተው መምራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
በፈረንጆቹ ሰኔ 2020 በተደረገው የእጅ ለእጅ ጦርነት 20 የህንድ እና አራት የቻይና ወታደሮች በሰሜን ሂማሊያን ላዳክ ከተገደሉ በኋላ ሁለቱም ሀገራት በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን በድንበር ላይ አሰፍረዋል። በከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች መካከል የተደረገ ውይይት ብዙም መሻሻል አላሳየም።
የሕንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብሃማንያም ጃሻንካር ከዋንግ ዪ ጋር ለሶስት ሰዓታት የፈጀውን ቆይታ ካደረጉ በኋላ መግለጫ በሰጡት መግለጫ “ከቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ባደረግኩት ውይይት በተለይም ሀገራዊ ስሜታችንን በማስተላለፍ ረገድ በጣም ግልጽ ነበርኩ” ብለዋል፡፡
ከፈረንጆቹ ሚያዚያ 2020 ጀምሮ ቻይና በድንበር አካባቢ ወታደር ማሰማራቷን ተከትሎ የተፈጠሩ ውጥረቶች በሁለቱ ሀገራት መካከል መደበኛ ግንኙነት ለመጀመር አስቸጋሪ እንደሚያደርጉ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
ዋንግ በመግለጫቸው ቻይና እና ህንድ በአለም ዙሪያ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን በጋራ መስራት አለባቸው ብለዋል።
"ሁለቱም ወገኖች... በድንበር ጉዳይ ላይ ያሉ ልዩነቶችን በሁለትዮሽ ግንኙነት ውስጥ በተገቢው ቦታ ላይ በማስቀመጥ የሁለትዮሽ ግንኙነት ትክክለኛ የእድገት አቅጣጫን መከተል አለባቸው" ብለዋል።
ቻይና ‘ዩኒፖላር ኤሺያ” እየተባለ የሚጠራውን አካሄድ እንደማትቀበል እና ሀቀጣናው ህንድ ያላትን የቆየ ሚና እንድትወጣ እንደምትፈልግ ገልጸዋል፡፡ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዩ ቻይና እና ህንድ ለአለም ሰላም መስፈን በጋራ መስራት አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በቤጂንግ የቀድሞ አምባሳደር ጃሻንካር ህንድ የዋንግ ጉዞን ባለፈው ሐሙስ መገባደጃ ላይ ዋና ከተማዋ ከመድረሱ በፊት ያላሳወቀችው በቻይና ጥያቄ ነው ብለዋል። ቻይና ወታደሮቿን ከድንበር አካባቢ ብታስወጣ፤ ህንድ እንድምታስወጣ አልታወቀም፡፡
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋንግ የድንበር ጉዳይን ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወደ መደበኛ አስተዳደር በፍጥነት እንዲሸጋገር ጠይቀዋል።
ቀሪ ጉዳዮችን በፍጥነት ለመፍታት፣በመሬት ላይ ያለውን ሁኔታ በአግባቡ ለመምራት እና አለመግባባቶችን እና የተሳሳቱ ሂሳቦችን ለማስወገድ ሁለቱም ተስማምተዋል ሲል አክሏል።