ሜንግ ለ1ሺ ቀናት በካናዳ በቁም እስር ላይ ቆይታለች
የቻይና ሚዲያዎችን ጠቅሶ ሮይተርስ እንደዘገበው በካናዳ ለ1ሺ ቀናት በቁም እስር ላይ የነበረችው እና የግዙፉ ቴሌኮሙኒኬሽን ኩባንያ ህዋዌ ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበረችው ሚንግ ዋንዙ በሀገሯ ቻይና ስትባ አቀባበል ተደርጎላታል፡፡
የቻይና መንግስት ሜንድ ታስራ የነበረው ባንክ ባቀረበው መሰረተ ቢስ ክስ ነው ሲል ቆይቷል፡፡ ነገርግን መንግስት በቻይና ታስረው ስለነበሩትና ለውጥ በሚመስል ምልኩ ከቻይና እስር ቤት ስለተለቀቁት ሁለት ካናዳውያን ዜጎች ዝምታ መርጧል፡፡
ሲሲቲቪ የተባለውን የቻይና ሚዲያ ጠቅሶ ሮይተርስ እንደዘገበው የህዋዌ ስራ አስፈጻሚ ሜንግን የያዘው አውሮፕላን የአሜሪካን የአየር ክልል በመተው በኖርዝ ፖል በኩል መብረሯን የሚጠቅስ መግለጫ አውጥቷል፡፡
ሜንግ ወደ ሀገሯ ቻይና ስትቃረብ አይኖቿ በእንባ እንደተሞሉ ተናግራለች፡፡ ሚንግ “ትልቅ ሀገር ባትኖረኝ ኖሮ፣ ዛሬ ያገኘሁትን ነጻነት አላገኝም ነበር” ብላለች፡፡
ሜንግ በካናዳ ቫንኮቨር በፈረንጆቹ 2018 ዓ.ም የተያዘችው፤ የኒው ዮርክ ፍርድ ቤት የአሜሪካን ማእቀብ በመጣስ ከህዋዌ ጋር ግንኙነት ያላቸው ኩባንያዎች ለኢራን መሳሪያዎችን ለመሸጥ ያደረጉትን ጥረት ሸፍነዋል በሚል የእስር ማዘዣ ማውጣቱን ተከትሎ ነበር፡፡
ከሁለት አመት የህግ ክርክርና ከአሜሪካ አቃቤ ህግ ጋር በተደረገ ስምምነት በኋላ ተለቃ ካናዳን ለቃ ወደ ትውልድ ሀገሯ ቻይና መመለስ ችላለች፡፡
ሜንግ ከታሰረች ከቀናት በኋላ በቻይና ባለስልጣናት የታሰሩት ካናዳያውያኑ ሚካኤል ኮቪሪግና ሚካኤል ስፓቮር ከእስር ተፈትተዋል፡፡ ሜንግ ከእስር የተፈታችው የቻይና መንግስት ባደረገው ከፍተኛ ጥረት መሆኑን ዠንዋን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡