ቻይና በቅርቡ የሞከረችው “YJ-21” ሃይፐርሶኒክ ሚሳዔል
ሚሳዔሉ አውዳሚ የጦር አረርን ተሸክሞ እስከ 1500 ኪ.ሜ ርቀት ውስጥ የሚገኝ ኢላማን ማጥቃት ይችላል
ሚሳዔሉ አውዳሚ የጦር አረርን ተሸክሞ እስከ 1500 ኪ.ሜ ርቀት ውስጥ የሚገኝ ኢላማን ማጥቃት ይችላል
ቻይና አዲስ እና እጅግ በጣም ፈጣን የተባለለት አዲስ ሃይፐርሶኒክ ሚሳዔል ማስወንጨፏ ተስመቷል።
ቻይና “YJ-21” ሃይፐርሶኒክ ሚሳዔል ባሳለፍነው ሳምንት ሩሲያ ሳርማት የተባለውን ሚሳዔሏን ከከሞከሯ አንድ ቀን ቀደም ብላ ማስወንጨፏም ተነግሯል።
አዲሱ የቻይና “YJ-21” ሃይፐርሶኒክ ሚሳዔል “ታይፕ 055” ከተባለ የጦር መርከብ ላይ መወንጨፉም ነው የወጡ መረጃዎች የሚያመላክቱት።
ቻይና አዲስ የሞከረችው ሚሳዔል ፀረ መርከብ ነው የተባለ ሲሆን፤ ሙከራውም ለአሜሪካ እና ለታይዋን አዲስ የራስ ምታት ነው ተብሏል።
“YJ-21” ሃይፐርሶኒክ ሚሳዔል እጅግ በጣም ፈጣን ነው የተባለ ሲሆን፤ ለመገመት አዳጋች የሆነ የበረራ ፍጥነት ፓተርን አንደሚጠቀምም ታውቋል።
ሚሳዔሉ እስከ 1 ሺህ 500 ኪሎ ሜትር ርቀት ውስጥ የሚገኝ ኢላማን መምታት እና ማውደም ይችላል የተባለ ሲሆን፤ ከባድ እና አደጋኛ የሆኑ የጦር መሳሪያ አረሮችን መሸከም የሚችል ነው።
“YJ-21” ሃይፐርሶኒክ ሚሳዔል ጥቃት የሚያደርስበት ክልል መጠን ከአዲሱ የአሜሪካ ኤፍ-35s የሚበልጥ መሆኑንም ነው የተገለፀው።
አዲሱ የቻይና “YJ-21” ሃይፐርሶኒክ ሚሳዔል ከአውሮፕላን ላይ በመወንጨፍ መሬት ላይ እንዲሁም በውኃ ላይ ያለ የጦር መርከብን ሊያወድም የሚችል ነው።
ቻይና በቅርቡ ጄ-20 (J-20) የተባለ ዘመናዊ ተዋጊ ጄቶቿን ለቁጥጥር ስራ ወደ ምስራቅና ደቡብ ቻይና ባህር ላይ ማሰማራቷን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን መዘገባው ይታወሳል።
በሰዓት እስከ 2 ሺህ 100 ኪሎ ሜትር ድረስ መብረር ይችላል የተባለለት “J-20” ተዋጊ ጄት፤ 19 ሺህ 390 ኪሎ ግራም ክብደት አለው ተብሏል።
በአሁኑ ወቅት 200 J-20 ተዋጊ ጄቶች የቻይና ህዝቦች ነጻነት ሰራዊት ተብሎ በሚጠራው የቻይና ጦር አየር ኃይል አገልግሎት እየሰጡ ነው።