የሩሲያ እና ቻይና ወዳጅነት የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምሳሌ ነው ተባለ
ሁለቱ አገራት የጎረቤት እና ወዳጅነት ስምምነትን ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት አራዝመዋል
የቻይና እና ሩሲያ ፕሬዘዳንቶች በበይነ መረብ ታግዘው ውይይት አድርገዋል
የሩሲያ እና የቻይና ወዳጅነት የ21ኛው ክፍለ ዘመን የትብብር ምሳሌ መሆኑን ፕሬዘዳንት ፑቲን ተናገሩ፡፡
የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ከሩሲያ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር የበይነ መረብ ውይይት አድርገዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ብላድሚር ፑቲን ከውይይቱ በኋላ እንዳሉት የቻይና እና ሩሲያ አሁናዊ ወዳጅነት የ21ኛው ክፍለ ዘመን አርዓያ ነው፡፡
ኔቶ በዩክሬን ጉዳይ ቀይ መስመር ካለፈ ሩሲያ እርምጃ ትወስዳለች- ፕሬዝዳንት ፑቲን
ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ በበኩላቸው የሁለቱ አገራት ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት በብዙ መስኮች ስኬታማ እንደነበር ተናግረዋል፡፡
ቻይና፤ የቡድን 7 አባል ሀገራት “ዓለምን መናቅ” አይችሉም አለች
ሁለቱ አገራት የጋራ ጥቅሞቻቸውን እና ፍላጎቶቻቸውን የሚጎዱ ነገሮችን በጋራ ሲመክቱ መቆየታቸውን የተናገሩት ጂንፒንግ ሩሲያ ይህ እንዲሆን ላደረገችው ጥረት ምስጋናም አቅርበዋል፡፡
ሩሲያ እና ቻይና የጉርብትና እና ወዳጅነት ስምምነትን ከ20 ዓመት በፊት ተፈራርመው ወደ ስራ የገቡ ሲሆን ይሄንን ስምምነት በአምስት ዓመታት ለማራዘም መስማማታቸው ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል፡፡
ቻይና እና ሩሲያ በወታደራዊ፣ በቴክኖሎጂ፣ በጠፈር ሳይንስ፣ ንግድ እና ኢንቨስትመንትን ጨምሮ በሌሎች ሁለትዮሽ እና ዓለም አቀፋዊ አጀንዳዎች ዙሪያ በመስራት ላይ ናቸው፡፡
የሁለቱ አገራት የንግድ እና ኢንቨስትመንት መጠን አሁን ላይ ከ100 ቢሊዮን ዶላር በላይ የደረሰ ሲሆን በፈረንጆቹ 2024 ዓመት ደግሞ በእጥፍ የማሳደግ ፍላጎት አላቸው፡፡
ሁለቱ አገራት በሀይል ልማት በጋራ በመስራት ላይ ሲሆኑ ቻይና ከሩሲያ ነዳጅን ወደ አገሯ ለማጓጓዝ የ400 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት ፈጽማ ግንባታውን በማፋጠን ላይ ትገኛለች፡፡