ከቱርክ እና ሶሪያ ርዕደ መሬት በአስገራሚ ሁኔታ የተረፉ ሰዎች በምስል
ከ24 ሺህ በላይ የነፍስ አድን ስራተኞችን ወደ ስራ ያስገባችው ቱርክ እስካሁን ከ8 ሺህ በላይ ሰዎችን ከፍርስራሽ ውስጥ ማውጣት መቻሏ ተገልጿል
የተለያዩ መገናኛ ብዙሃንም በአስደናቂ ሁኔታ ህይወታቸው የተረፈ ህጻናት እና አዛውንቶችን ምስል እያጋሩ ይገኛሉ
በቱርክና ሶሪያ በደረሰው አሰቃቂ ርዕደ መሬት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር በየጊዜው እያሻቀበ ነው።
ቱርክ ዛሬ ማለዳ ያወጣችው መረጃ እንደሚያሳየው የሟቾቹ ቁጥር 6 ሺህ 234 መድረሱን ያሳያል።
አደጋው ከደረሰ ሶስተኛ ቀኑን መያዙን ተከትሎ በፍርስራሽ ውስጥ ህይወታቸው ያለፈ ግን ያልተደረሰባቸው በርካቶች እንደሚሆኑ ተሰግቷል።
ከ24 ሺህ በላይ የነፍስ አድን ስራተኞች ግን አሁንም ርብርባቸውን ቀጥለዋል።
የተለያዩ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንም ከሁለት እና ሶስት ቀናት በኋላ ህይወታቸው በተአምር የተረፈ ህጻናት እና አዛውንቶችን ምስል እያጋሩ ይገኛሉ።
ቱርክ እስካሁን ከ8 ሺህ በላይ ሰዎችን ከፍርስራሾች ውስጥ ማውጣት ችላለች።
ከሁለት ቀን በላይ በፍርስራሽ ውስጥ የቆዩ ህጻናት እና ታዳጊዎች ከፍርስራሾች እንዲወጡ ሲደረግ ልዩ ስሜትን ፈጥሯል።
አደጋው በደረሰ እለት የወለዱ አራስ እናቶች እና ጨቅላ ህጻናትም በተአምር ተርፈዋል።
በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው ከ37 ሺህ በላይ ሰዎች ቆስለዋል።
ከ11 ሺህ በላይ ህንጻዎችን ማፈራረሱ የተነገረለት ርዕደ መሬት የሺዎችን ህይወት ከመቅጠፉ ባሻገር በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ቤት አልባ አድርጓል።
በባብር ጣቢያዎች እና ተሽከርካሪዎች ውስጥ የሚተኙት በርካታ ናቸው።
በሶሪያም የሟቾቹ ቁጥር በዛሬው እለት ከ2 ሺህ 400 በላይ መድረሱ ተነግሯል።