ልዩልዩ
ቻይና ታሪካዊ በተባለ ተልዕኮ ስድስት ጠፈርተኞች ህዋ ላይ አሰማራች
በቻይናው ሼንዙ 15 የጠፈር መንኮራኩር ላይ የተሳፈሩ ሦስቱ ጠፈርተኞች ረቡዕ ከሌሎች የጠፈር ተመራማሪዎች ጋር ተገናኝተዋል
ጠፈርተኞቹ በጣቢያው ለስድስት ወራት ይቆያሉ ተብሏል
ቻይና ታሪካዊ በተባለ ተልዕኮ ስድስት ጠፈርተኞችን ወደ ህዋ አሰማራች
በቻይና ሼንዙ 15 የጠፈር መንኮራኩር የተሳፈሩት ሦስቱ ጠፈርተኞች ወደ ሀገሪቱ የጠፈር ጣቢያ ገብተው ከሌሎች የጠፈር ተመራማሪዎች ጋር በመገናኘት ታሪካዊ ስብሰብ ፈጥረዋል ተብሏል።
ይህ ታሪካዊ ስብሰባ ለመጀመሪያ ጊዜ በምህዋር ላይ ባለው ቤተ-ሙከራ ውስጥ ያለውን የሰው ኃይል ወደ ስድስት ከፍ ማድረጉን ዥንዋ ዘግቧል።
የተልዕኮው ቡድን እሮብ ጠዋት ወደ ቲያንጎንግ የጠፈር ጣቢያ ገብቷል።
የሼንዙ 15 የጠፈር መንኮራኩር ከመሬት በላይ 400 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ዝቅተኛ የምድር ምህዋር ላይ ከቲያንጎንግ ጣቢያ መድረሷ ታውቋል።
ሦስቱ የሼንዡ 15 ጠፈርተኞች በቻይና የጠፈር ጣቢያ ከሦስቱ የሼንዙ 14 ጠፈርተኞች ጋር ተገናኝተዋል።
የቻይና ምህዋር ጣቢያ ለመድረስ ጠቅላላ ሂደቱ ስድስት ሰዓት ከ50 ደቂቃ እንደወሰደ ሲጂቲኤን ዘግቧል።
የተልዕኮው አባላት ፊ ጁንሎንግ፣ ዴንግ ኪንግሚንግ እና ዛንግ ሉ ሲሆን፤ በጣቢያው ለስድስት ወራት ይቆያሉም ተብሏል።