መጸዳጃ ቤት ረጅም ሰዓት የሚቆዩ ሰራተኞቹን የሚያሸማቅቀው ተቋም
ተቋሙ በመጸዳጃ ቤት ውስጥ ካሜራ ገጥሟል ተብሏል
በመጸዳጃ ቤት ውስጥ ሲጋራ የሚያጨሱ እና ጌም የሚጫወቱትን ሰራተኞች በአደባባይ ፎቷቸውን መለጠፉም ተገልጿል
መጸዳጃ ቤት ረጅም ሰዓት የሚቆዩ ሰራተኞቹን የሚያሸማቅቀው ተቋም
እርስዎ በሚሰሩበት ተቋም ውስጥ ሲጸዳዱ በድንገት ካሜራ ተገጥሞ ቢያዩ ምን ይላሉ?
በሀገረ ቻይና አንድ ኩባንያ በመጸዳጃ ቤት ውስጥ ሁነቶችን ለመከታተል ካሜራ ገጥሞ ተገኝቷል፡፡
ኩባንያው የሁነት መከታተያ ካሜራ የገጠመው ሰራተኞች መጸዳጃ ቤት ውስጥ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ለመከታተል መሆኑን አስታውቋል፡፡
እንደ ኩባንያው አስተያየት ከሆነ መጸዳጃ ቤት ውስጥ በመግባት ረጅም ሰዓት የሚቆዩ፣ ሲጋራ የሚያጨሱ፣ ጌም የሚጫወቱ እና መሰል ድርጊቶችን የሚፈጽሙ ሰራተኞች አሉ ብሏል፡፡
በዚህ ምክንያት ሰራተኞች ረጅም ጊዜያቸውን መጸዳጃ ቤት ውስጥ እየገቡ በመቆየታቸው ኩባንያው ተበድሏል የሚለው ይህ ተቋም መሰል ተግባራትን የሚያደርጉ ሰራተኞችን ለመለየት ካሜራውን እንዳስገጠመ ተናግሯል፡፡
በመጸዳጃ ቤት ውስጥ ረጅም ሰዓት የሚቆዩ ሰራተኞችን ፎቶ በግልጽ የድርጅቱ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ እንደሚለጥፍም ኦዲቲ ሴንትራል የቻይና ሚዲያዎችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡
ይህን ተከትሎ ሰራተኞች መብታችን ተገፏል፣ ፎቷችን በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ያለፈቃዳችን ተለጥፏል ይህ መሆኑ ደግሞ እንድንሸማቀቅ አድርጎናል ሲሉ ጉዳዮን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ያጋሩ ሲሆን በርካቶች መነጋገሪያ አጀንዳ አድርገውታል፡፡
ኩባንያው በሰጠው ምላሽ መጸዳጃ ቤት ውስጥ እየገቡ የስራ ሰዓትን የሚበድሉ ሰራተኞች በመኖራቸው ነው ይህንን ያደረኩት ሲል ገልጿል፡፡