“የአሜሪካ ፖለቲከኞች የ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ሕዝብ ጠላት መሆን አምሯቸዋል”- ቻይና
የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፤ ናንሲ ፔሎሲ “ቢሊዮን ጠላቶችን እያፈራች ነው” ብለዋል
የአሜሪካ አፈጉባኤ ታይዋንን እጎበኛለሁ ማለታቸውን ተከትሎ በሩቅ ምስራቅ ውጥረት ነግሷል
የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፤ የተወሰኑ የአሜሪካ ፖለቲከኞች የቻይና ሕዝብ ጠላት መሆን መፈለጋቸውን አስታወቁ፡፡
ሚኒስትሩ ዋንግ ይ የአሜሪካ አፈጉባዔ “ቢሊዮን ጠላቶችን እያፈሩ ነው” እንደሆነም ተናግረዋል።
- በተመድ የቻይና መልዕክተኛ፤ የአሜሪካ ባለስልጣን ታይዋንን ለመጎብኘት ማቀዳቸው “ነገር ፍለጋ” ነው አሉ
- ሩሲያ የፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት እቅድ “ትንኮሳ” ነው ስትል አሜሪካን አስጠነቀቀች
ሚኒስትር ዋንግ ይ ይህንን ያሉት የአሜሪካ አፈ ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ ወደ ታይዋን ያደርጉታል የተባለውን ጉብኝት በተመለከተ ነው።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የቻይና ልዩ መልዕክተኛ በአፈጉባኤዋ የታይዋን ጉዞ ዙሪያ ምላሽ መስጠታቸውን የተገለጸ ሲሆን አሁን ደግሞ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተመሳሳይ ይዘት ያለው አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
በተመድ የቻይና ልዩ መልዕክተኛው ሃንግ ጁን፤ የአፈጉባዔዋ ጉብኝት እጅግ አደገኛ መሆኑን የገለጹ ሲሆን ዋንግ ይ ደግሞ የተወሰኑ የአሜሪካ ፖለቲከኞች የቻይና ሕዝብ ጠላት መሆን ፈልገዋል ብለዋል።
አሁን ላይ ወደ ታይዋን እንደሚሄዱ የሚጠበቁት ናንሲ ፔሎሲ ቢሊዮን ጠላቶችን እያፈሩ ነው ሲሉም ነው ዋንግ ይ ያስታወቁት።
የአሜሪካ ፖለቲከኞች የ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ሕዝብ ጠላት ለመሆን ፈልገዋል ነገር ግን ጥሩ ውጤት እንደማያመጡ እርግጠኞች ነን ሲሉም ነው ዋንግ ይ የተናገሩት።
የአሜሪካ አፈ ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ ወደ ታይዋን ያደርጉታል የተባለው ጉዞ በዋሸንግተንና በቤጅንግ መካከል ጦርነት እንዳይቀሰቅስ ተሰግቷል።
የአሜሪካ አፈ ጉባኤ ናንሲ ሌሎሲ ታይዋንን ጨምሮ አምስት የእስያ ሀገራትን ጉብኝት መጀመራቸውን ተከትሎ ዓለም አይኑ ታይዋን ላይ አርፏል።
ቻይና በአሜሪካ ፖለቲካ ሶስተኛው የስልጣን ባለቤት እየሆኑት ናንሲ ፔሎሲ ታይዋንን ከጎበኙ እርምጃ እወስዳለሁ ማለቷን ተከትሎ በሩቅ ምስራቅ ውጥረት ነግሷል።
ይሄንን ተከትሎም አስቀድማ ናንሲ ፔሎሲ ታይዋንን ከጎበኙ እርምጃ እወስዳለሁ ያለችው ቻይና የአየር እና የባህር ሀይል ጦሯን ወደ ታይዋን አቅርባለች።
የታይዋን መንግስትም ለሶስት ቀናት የሚቆይ የአደጋ መቋቋም ሀይሏን እንዳዘጋጀች አስታውቃለች።