ቻይና ወታደራዊ እርምጃ እወስዳለሁ ማለቷን ተከትሎ የአሜሪካ ጦር ወደ ታይዋን ቀርቧል
የታይዋን መንግሰት ድረ ገጽ በመጠለፉ ምክንያት ስራ ማቆሙ ተስመቷል።
የአሜሪካ አፈጉባኤ ታይዋንን እጎበኛለሁ ማለታቸውን ተከትሎ በሩቅ ምስራቅ ውጥረት ነግሷል።
አፈ ጉባኤ ናንሲ የሲንጋፖር ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ ታይዋን እንደሚገቡ የታይዋን መንግስታዊ እና የግል ብዙሀን መገናኛዎች በመዘገብ ላይ ናቸው።
የአውሮፕላን በረራውችን መረጃ በመስጠት የሚታወቀው ፍላይት ራዳር 24 የተሰኘው ተቋም ናንሲ ፔሎሲን የሚያጓጉዘው አውሮፕላን የበረራ አቅጣጫው ወደ ታይዋን እንደሆነ ጽፏል።
ይሄንን ተከትሎም የታይዋን መንግስት ድረገጽ ወይም ዌብሳይት ከታይዋን መንግስት ቁጥጥር ውጪ መሆኑን አርቲ ዘግቧል።
አስቀድማ ናንሲ ፔሎሲ ታይዋንን ከጎበኙ እርምጃ እወስዳለሁ ያለችው ቻይና የአየር እና የባህር ሀይል ጦሯን ወደ ታይዋን አቅርባለች።
የታይዋን መንግስትም ለሶስት ቀናት የሚቆይ የውጊያ መቋቋም ሀይሏን እንዳዘጋጀች አስታውቃለች። ይህ የውጊያ መቋቋም ዝግጁነት ሀይል ከዛሬ ጀምሮ እስከ ቀጣዩ ሀሙስ ድረስ እንደሚቆይ ተገልጿል።
በቻይናው ግሎባል ታይምስ ላይ ትንታኔዎችን በመጻፍ የሚታወቀው ሁ ጂያን የአሜሪካ ወታደራዊ አውሮፕላኖች ናንሲ ፔሎሲን አጅበው ወደ ታይዋን ለማስገባት ካሰቡ ይህ አሜሪካ በግልጽ በቻይና ላይ ወረራ እንደፈጸመች ይቆጠራል።
የቻይና ጦርም አውሮፕላኑን መምታት እንዳለበት በትዊተር ገጹ አስፍሯል።
የአሜሪካ እና ቻይና የጦር አውሮፕላኖች እና የባህር ላይ ወታደሮቻቸውን ወደ ታይዋን አቅርበዋል።