ቻይና ፔሎሲ ታይዋን የምትጎበኝ ከሆነ “ጦሯ ዝም ብሎ እንደማይቀመጥ” ቀድም ብላ አስጠንቅቃለች
ሩሲያ የአሜሪካ አፈጉባኤ ቃል አቀባይ ናንሲ ፔሎሲ ያደርጉታል የተባለው የታይዋን ጉብኝት ትንኮሳ ነው ስትል አሜሪካን አስጠንቅቃለች፡፡
ሩሲያ የፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት ታይዋን ከቻይና ጋር የሚያጋጭ በቀጣናው ውጥረት የሚያነግስ ነው ማለቷን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
“አሁን ላይ ፔሎሲ ታይዋን ትጎበኛለች ወይም አትጎበኝም የሚለውን ርግጠኛ ሆኖ መናገር አይቻልም፤ ነገርግን ይደረጋል የተባለው ጉብኝት ፍጽም ትንኮሳ ነው “ ብለዋል የክሬሚሊን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ፡፡
ቻይና የአሜሪከዋ አፈጉባኤ የራሷ ግዛት አካ አድርጋ ወደምታያት ታይዋን እንዳይሄዱ ቀደም ብላ አስጠንቅቃለች፡፡
የፔሎሲ ጉብኝት አሜሪካ አከብረዋለሁ የምትለው የአንድ ቻይና ፖሊስ የሚቃረን ነው ብላለች ቻይና፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ቻይና፤የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ ታይዋንን የሚጎበኙ ከሆነ ጦሯ “ዝም ብሎ እንደማይቀመጥ”ቻይና ማስጠንቀቂያ አስተላልፋለች፡፡
የአፈጉባኤዋ የሩቅ ምስራቅ ሀገራት የመጎብኘት ጉዞ ሲንጋፖርን፣ ማሌዥያን ፣ ደቡብ ኮሪያንና ጃፓን እንደሚያካትትም ነበር አፈጉባዔዋ የገለጹት፡፡ ታይዋን ከጉብኝት ዝርዝራቸው ውስጥ ያሶጡት ፔሎሲ፣አሁን ታይዋን ሊጎበኙ ይችላሉ የሚል ግምት አለ፡፡