በንቅሳቱ ምክንያት ህይወቱ የተመሰቃቀለበት ወጣት
ግለሰቡ በፊቱ እና ራስ ቅሉ ላይ የተነቀሰው ንቅሳት ሰርቶ እንዳይበላ አድርጎታል

መጥፎ ንቅሳት መሆኑን ዘግይቶ ያወቀው ይህ ወጣት ንቅሳቱን ለማጥፋት ከስቃይ ጋር ዓመታን ሊወስድበት ይችላል ተብሏል
በንቅሳቱ ምክንያት ህይወቱ የተመሰቃቀለበት ወጣት
በአጭሩ ሚስተር ኤ የሚል ስም ያለው የ24 ዓመት ወጣት ቻይናዊ ከዓመታት በፊት የተነቀሰው ንቅሳት ህይወቱን አክብዶበታል ተብሏል፡፡
ወጣቱ በተለይም ከስድስት ዓመታት በፊት በፊቱ እና ራስ ቅሉ ላይ የተነቀሰው ንቅሳት ህይወቱን እንዳከበደበት ለቻይናው ሞርኒነግ ፖስት ተናግሯል፡፡
ስራ ለመቀጠር ወደ ቀጣሪ ተቋማት ሲያመራ ከፈተና እና ቃለ መጠይቅ አስቀድመው ሊቀጥሩኝ እንደማይችሉ ይነግሩኛል ብሏል፡፡
በፊቱ ላይ ያለው ንቅሳት የስራ ውሎችን እና የባንክ ሂሳብ መክፈት እንዳይችል አድርጎታል የተባለ ሲሆን ችግሩ ከራሱ አልፎ ቤተሰቡ ችግር ውስጥ እንዲገባ እንዳደረገው ተናግሯል፡፡
በዚህ ምክንያት ህይወቱ መክበዱን የሚናገረው ይህ ወጣት ንቅሳቶቹን ለማጥፋት ያደረገው ሙከራ ለከባድ ህመም እንደዳረገውም አክሏል፡፡
ከአውሮፓ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ በፊት የእንግሊዝን አሸናፊነት የሚገልጽ ንቅሳት የተነቀሰው እንግሊዛዊ
በተለይም በአይኑ እና ራስ ቅሉ ላይ የተነቀሳቸውን ንቅሳቶች ለማጥፋት ቢሞክርም ከባድ ስቃይ ውስጥ እንዲገባ እና በዚሁ ከቀጠለ የአይን ብርሃኑን ሊያጣ እንደሚችል ተነግሮታል ተብሏል፡፡
በመሆኑም በቀጣዮቹ ዓመታት በፊቱ ላይ እና ራስ ቅሉ ላይ ያሉ ንቅሳቶችን ለማጥፋት ተከታታይ ጥረቶችን እንደሚያደረግ ገልጿል፡፡
የንቅሳት ባለሙያዎች በበኩላቸው ንቅሳቶቹ ከባድ እና በቀላሉ ማጥፋት የማይቻሉ ናቸው ያሉ ሲሆን በተለይም አይኖቹ አካባቢ ያሉት ደማቅ ጥቁር ቀለም ያላቸውን ንቅሳቶች ለማጥፋት ረጅም ጊዜ እና ጥንቃቄ የሚፈልጉ ናቸውም ብለዋል፡፡