ቻይና የጃፓንን የአየር ክልል ለመጀመሪያ ጊዜ መጣሷን ተከትሎ ጃፓን ከፍተኛ ቁጣ አሰማች
የጃፓን ጄቶች ድንበር ጥሰው የገቡትን የቻይና ጄቶች ወዲያውኑ እንዲመለሱ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋቸዋል ተብሏል
ጃፓን በቅርብ አመታት ውስጥ ቻይና በጃፓን ዙሪያ የምታደርጋቸው ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች "እየተስፋፉ እና እየጨመሩ" ናቸው ብላለች
ቻይና የጃፓንን የአየር ክልል ለመጀመሪያ ጊዜ መጣሷን ተከትሎ ጃፓን ከፍተኛ ቁጣ አሰማች
የቻይና የጦር ጄት የጃፓንን የአየር ክልል መጣሱን የተናገሩት የቻይና መንግስት ቃል አቀባይ ክስተቱን "በፍጹም ተቀባይነት የሌላው" የግዛት ጥሰት እና የደህንነት ስጋት ሲሉ ገልጸውታል።
የቻይና ዋና የካቢኔ ጸኃፊ የሆኑት ዮሺማሳ ሀያሺ ዋይ-9 የተባለው የቻይና የቅኝት አውሮፕላን በትናንትናው እለት የጃፓንን ደቡባዊ የአየር ክልል መጣሱን እና ይህም የጦር ጄቶቿ ምላሽ ለመስጠት እንዲጣደፉ እንዳደረጋቸው ተናግረዋል። ጸኃፊው እንደተናገሩት የጃፓን መከላከያ ኃይል የቻይና የጦር ጄት የጃፓንን የአየር ክልል ጥሷል ብሎ ሪፖረት ሲያደርግ ይህ የመጀመሪው ነው።
"የቻይና ወታደራዊ ጄት የጃፓንን የአየር ክልል መጣሱ ከባድ የግዛት ጥሰት ብቻ ሳይሆን የደህነት ስጋትም ነው" ሲሉ ሀያሺ ተናግረዋል። "ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ሆኖ አግኝተነዋል።"
ዋይ-9 የተባለው የቻይና የቅኝት የጦር አውሮፕላን በደቡባዊ ጃፓን በሚገኘው ዳንጆ ደሴት ላይ ለሁት ደቂቃ ያህል መዞሩን የገለጸው የጃፓን መከላከያ ኃይል ባለስልጣናት ሁነቱን እየገመገሙት መሆኑን አክሎ ገልጿል።
የጃፓን ጄቶች ድንበር ጥሰው የገቡትን የቻይና ጄቶች ወዲያውኑ እንዲመለሱ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋቸዋል ተብሏል።
ሀያሺ እንደገለጹት ከሆነ በቅርብ አመታት ውስጥ ቻይና በጃፓን ዙሪያ የምታደርጋቸው ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች "እየተስፋፉ እና እየጨመሩ" ናቸው።
ሀያሺ ጃፓን የቻይናን ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንደምትከታተል እና ሊኖሩ ለሚችሉ የአየር ክልል ጥሰቶች አስፈላጊውን ምላሽ እንደምትሰጥ ተናግረዋል። የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሩ ማሳታካ ኦካኖ የአየር ጥሰቱን ለመቃወም የቻይና አምባሳደር ተወካይን ሺ ዮንግን ጠርተዋል ብሏል።
ኦካኖ ቻይና ይህን አይነት ድርጊት ከመውሰድ እንድትታቀብም ጠይቀዋል።