ከቁጥጥር ውጭ የሆነችው የቻይና ሮኬት በመጪዎቹ ሁለት ቀናት ምድር ላይ ልትወድቅ እንደምትችል ተገለፀ
18 ቶን ክብደት ያለው የሮኬቷ አካል በሰዓት 28 ሺህ ኪሎ ሜትር ገደማ ወደ ምድር እየተምዘገዘገ ነው ተብሏል
የሮኬቷ ግዙፍ አካል ነገ ቅዳሜ አሊያም በቀጣዩ ቀን እሁድ መሬት ላይ ሊወድቅ እንደሚችል ተገምቷል
ከቁጥጥር ውጭ የሆነችው የቻይና ‘Long March-5B’ ሮኬት አካል በመጪዎቹ ሁለት ቀናት ውስጥ ምድር ላይ ሊወድቅ እንደሚችል ይጠበቃል።
ሮኬቷ ባሳለፍነው ወር ከአዲሱ ‘ቻይና የጠፈር ማእከል’ ወደ ጠፈር የተላከች ሲሆን ፣ ወደ ምድር ለመመለስ የምታደርገው ጉዞ ግን ከቁጥጥር ውጭ መሆኑ ነው የተነገረው።
በአሁኑ ወቅትም 18 ቶን ክብደት ያለው የሮኬቷ አካል በሰዓት 28 ሺህ ኪሎ ሜትር ገደማ ወደ ምድር እየተምዘገዘገ መሆኑንም ነው መረጃዎች የሚያመለክቱት።
ወደ ምድር በመምዘግዘግ ላይ የምትገኘው ሮኬቷ ነገ ቅዳሜ አሊያም እሁድ መሬት ላይ ልትወድቅ እንደምትችል ነው ግምቶች የሚያመላክቱት።
ምድራችን በብዛት በውሃ የተሸፈነች እንደመሆኗ የሮኬቷ አካል በውቅያኖስ ላይ የመውደቅ እድሉ የሰፋ መሆኑ ነው የተነገረው።
ሆኖም ግን ሰዎች የሚኖሩበት መሬት ላይ መውደቅ እድሎሉ ዜሮ ነው ለማልት አይቻልምም ብለዋል የዘርፉ ተመራማሪዎች።
ጆናታን ማክዶዌል የተባሉ የአሜሪካ የጠፈር ተመራማሪ ከሲ.ኤን.ኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ የሮኬቱ አካል የት ሊወድቅ እንደሚችል ከአሁኑ መገመት አይቻልም ብለዋል።
ተመራማሪው ጉዳዩ የሚያሳስብ እንዳልሆነም ነው ተናገሩት።
የቻይና የመንግስት ሚድያዎች በበኩላቸው የሮኬቷ የውጭ አካል በቀጭን የአልሙኒየም ብረት የተሸፈነ እና በቀላሉ የሚቀልጥ በመሆኑ ወደ ምድር ሳይደርስ ሊቀልጥ እንደሚችል እና በሰዎች እንዲሁም በንብረት ላይ የጎላ አደጋ እንደማያደርስ ዘግበዋል።