ምዕራባውያን ሀገራት ፑቲን ያሸነፉትን ምርጫ ነጻ እና ዲሞክራሲያዊ አይደለም በሚል ሲያወግዙት ቻይና እና ሰሜን ኮሪያ ግን ለፑቲን የደስታ መግለጫ አውጥተዋል
ፑቲን በአዱሱ የስልጣን ዘመናቸው የመጀመሪያ ጉብኝታቸውን በቻይና እንደሚያደርጉ ገለጹ።
ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የተደረገውን ምርጫ ያሸነፉት የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን በአዲሱ የስልጣን ዘመናቸው የመጀመሪውን የውጭ ጉብኝታቸውን በቻይና ለማድረግ እንዳሰቡ ተናግረዋል።
የቻይናው ኮሙኒስት ፓርቲ መሪ ገንዲ ዝዩጋኖብ ከፓርላማ አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት ፑቲን ቤጅንግን እንዲጎበኙ መጠየቃቸውን ሮይተርስ የሩሲያውን ታስን ጠቅሶ ዘግቧል።
ዝዩጋኖቭ "የመጀመሪያው ጉብኝትህ ወደ ምስራቅ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ።ጓድህ (የቻይናው ፕሬዝደነትት) ሺ ጂንፒንግ ሀገሩን እንድትጎበኝለት ይፈልጋል" ሲሉ ተያግረዋል።
ፑቲንም ጉብኝቱን ሊያደርጉ እንደሚችሉ ተናግረዋል።
ምዕራባውያን ሀገራት ፑቲን ያሸነፉትን ምርጫ ነጻ እና ዲሞክራሲያዊ አይደለም በሚል ሲያወግዙት ቻይና እና ሰሜን ኮሪያ ግን ለፑቲን የደስታ መግለጫ አውጥተዋል።
ፑቲን ሩሲያ ለቀጣይ ስድስት አመታት ሩሲያ ይመራሉ።
ፕሬዝደንት ፑቲን ከሁለት አመት በፊት በዩክሬን ላይ ልዩ ያሉትን ወታደራዊ ዘመቻ ከከፈቱ በኋላ ከምዕራባውያን ጋር ያላቸው ግንኙት በእጅጉ ሻክሯል። ምዕራባውያን ፑቲን ላሸነፉበት ምርጫ እውቅና ያለሰጡበት አንደኛው ምክንያት ይህ ሊሆን ይችላል።
ሩሲያ በምስራቅ ዩክሬን የምታደርገውን ጥቃት የቀጠለች ሲሆን በቅርቡ ወሳኟን አቭዲቪካ ከተማን ጨምሮ በርካታ መንደሮችን ቶጣጠራለች።
ዩክሬን የምዕራባውያን ወታደራዊ ድጋፍ በአፋጣኝ በላመድረሱ ቦታዎቹን ለመልቀቅ መገደዷን መግለጿ ይታወሳል።
ምዕራባውያን ለዩክሬን የጦር መሳሪያ ከማቅረብ አልፈው ጦር የሚልኩ ከሆነ ሶስተኛው የዓለም ጦርነት ይነሳል ስትል ሩሲያ አስጠንቅቃለች።