በአቧራ ልትዋጥ ጫፍ ላይ የደረሰችው ታሪካዊ ከተማ
ከ10 ዓመት በፊት የቤት ጣሪያ የነበሩ ቦታዎች አሁን ላይ የግመሎች መንገድ ሆኗል ተብሏል

ከተማዋ ከእስልምና ዕምነት ጋር በተያያዘ ታሪካዊ እና በርካታ ጥንታዊ ሰነዶች የሚገኙባትም ነበረች
በአቧራ ልትዋጥ ጫፍ ላይ የደረሰችው ታሪካዊ ከተማ
የአየር ንብረት ለውጥ በተለይም ድርቅ እጸዋትን በማድረግ ስነ ህይወትን በመጉዳት የሚታወቅ ቢሆንም ውቂያኖስን አድርቆ ወደ አሸዋነት ሲቀየር መመልከት ግን የተለመደ አይደለም፡፡
የሞሪታንያዋ ቺንጉቲ ከተማ በባህር ዳርቻ የምትገኝ ታሪካዊ ከተማ ነች፡፡ ዓለም አቀፉ የቅርስ ተቋም ዩኔስኮ በዚች ከተማ የሚገኙ አራት ቅርሶችን በዓለም ቅርስነትም መዝግቧል፡፡
ከተማዋ ከእስልምና ዕምነት ጋር በተያያዘ በርካታ ታሪካዊ ቅርሶችን የያዘች ሲሆን ከዕምነቱ ጋር የተያያዙ ጥናቶችን ለማድረግ ቁልፍ ከተማ እንደሆነችም ይገለጻል፡፡
ባንድ ወቅት የባህር ዳርቻ የነበረችው ይህች ከተማ አሁን ላይ የባህሩ ውሃ ደርቆ በአሸዋ የተተካ ሲሆን ከዚህ የሚነሳው አሸዋ ከተማዋን በአቧራ ክምር እየዋጣት ነው ተብሏል፡፡
ወደ ከተማዋ የሚገባው የአሸዋው አውሎ ነፋስ በየዓመቱ እየጨመረ መጥቶ አሁን ላይ ዋና ዋና መተላለፊያ መንገዶች እና መኖሪያ ቤቶች በአቧራ ክምር ተውጠዋል፡፡
ከዚህ በፊት የተምር ዛፎችን ጨምሮ አረንጓዴ ተክሎች በቅሉበት የነበሩ ቦታዎች አሁን ላይ ሁሉም ምድረ በዳ ሆኖ አረንጓዳ ተክል ማየት ብርቅ እንደሆነም ዩሮ ኒውስ ዘግቧል፡፡
እንደዘገባው ከሆነ ከዚህ በፊት የመኖሪያ ቤቶች ጣሪያ የነበሩ ቦታዎች አሁን ላይ የግመሎች መጓጓዣ መንገዶች ሆነዋል፡፡
ነዋሪዎችም ቀስ በቀስ ከተማዋን እየለቀቁ ወደ ሌሎች ከተሞች እየተሰደዱ ነው የጠባለ ሲሆን የሞሪታንያ መንግስት ከዓለም አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ተቋማት ጋር በመሆን ዛፍ ለመትከል የጀመረው ጥረት ሳይሳክ ቀርቷል ተብሏል፡፡
በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሞሪታንያ ካለው ጠቅላላ መሬት ውስጥ የሚታረሰው መሬት አንድ በመቶ እንኳን አይሞላም፡፡