ድርቅ ለምን ድሀ የዓለማችን ሀገራትን ያጠቃል?
በኢራቅ፣ ሶሪያ እና በኢራን የሚከሰተው ድርቅ ምንጩ የድንጋይ ከሰል እና ጋዝ ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል
ኢራን፣ ሶሪያ እና ኢራቅ በሰው ሰራሽ ድርቅ የተጠቁ ሀገራት ናቸው ተብለዋል
ድርቅ ለምን ድሀ የዓለማችን ሀገራትን ያጠቃል?
ዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ማህበር ባስጠናው ጥናት መሰረት ሶሪያ፣ ኢራን እና ኢራቅ በዓለም ከባዱን ድርቅ ያስተናግዳሉ።
ድርጅቱ አክሎም የአየር ንብረት ለዓለም ሙቀት መጨመር የቀጥታ አስተዋጽኦ አለው ያለ ሲሆን ይህም በሶሪያ እና በኢራቅ የድርቅ መጠኑን በ25 ጊዜ እንዲሁም በኢራን ደግሞ 16 ጊዜ እንዲከሰት መነሻ ሆኗል ብሏል።
ጥናቱ ከዚህ በተጨማሪም በሀገራቱ ያጋጠመው አለመረጋጋት ከደረሰባቸው ድርቅ በቶሎ እንዳያገግሙ ስለማድረጉም ጠቅሷል።
እነዚህ ድርቅ ከፍተኛ የሆነባቸው ሶስቱ ሀገራት አሁንም በድርቅ የመጠቃት እድላቸው ሰፊ ነው የተባለ ሲሆን ቢያንስ በ10 ዓመት አንዴ ክፉኛ ድርቅ ሊያጠቃቸው ይችላልም ተብሏል።
ቻይና አረብ ኢምሬትስ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ ገለጸች
ይህ ይከሰታልብየተባለው ድርቅ በአየር ንብረት ለውጥ ብቻ ሳይሆን በጋዝ እና ድንጋይ ከሰል ምክንያቶች ሊከሰት እንደሚችልም ተገልጿል።
ጥናቱ ከሀምሌ 2020 እስከ ሰኔ 2023 ድረስ ያሉ ክስተቶችን የዳሰሰ ሲሆን በነዚህ ዓመታት በተከሰተው ድርቅ ምክንያት እንደ ጢግረስ ኢፍራተስ የተሰኙ ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ድርቅ እንዲገጥማቸው አድርጓል ተብሏል።
በዚህ ድርቅ ምክንያትም ሶሪያ፣ ኢራቅ እና ኢራን መጎዳታቸው የጠቀሰው ይህ ጥናት ድርቁ ከተፈጥሮ ይልቅ በሰው ሰራሽ ምክንያቶች እንደደረሰ አስታውቋል።