ፕሬዝዳንት ማክሮን ድህነትን ለመዋጋትና የአየር ንብረትን ለመታደግ "የፋይናንስ ለውጥ" ጠየቁ
ማክሮን የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ድጋፍ "በቂ አይደሉም" ሲሉ ተችተዋል
የአየር ንብረት ቀውስን ለመቋቋምና ከድህነት ለመውጣት በትሪሊዮን የሚቆጠር ዶላር ያስፈልጋል ተብሏል
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በፓሪስ እየተካሄደ ባለው ጉባኤ ላይ ድህነትን ለመዋጋት እና የአየር ንብረትን ለመታደግ "አዲስ ዓለም አቀፍ ትብብር" እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንቱ ለዚህም "ህዝባዊ የገንዘብ ስርዓት ለውጥ" ጥሪ አቅርበዋል።
የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ደካማ ሀገራት የድህነት እና የአየር ሙቀት መጨመር ፈተናዎች ብቻቸውን እንዲጋፈጡ ላለማድረግ ሀገራት እና ተቋማት "የግል ፋይናንስን" የማሳደግ አዝማሚያ እንዲደግፉ አሳስበዋል።
"ሀገሮች ድህነትን የመዋጋት ወይም የአየር ንብረት ለውጥን የመዋጋት ምርጫ ሊገጥማቸው አይገባም" ያሉት ማክሮን፤ በጉባኤው መክፈቻ ወቅት ሁለቱን ችግሮች በአንድ ጊዜ መጋፈጥ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት የዓለምን ጊዜ የዋጀ "በህዝብ ፋይናንስን አስደንጋጭ ሁኔታ መቋቋም አለብን" እና "የግል ፋይናንስ የበለጠ ያስፈልገናል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
ማክሮን "በፍጥነት በበቂ ሁኔታ እየሰሩ አይደሉም" እና "በቂ አይደሉም" ሲሉ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማትን ተችተዋል።
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት "የሁሉንም ሉዓላዊነት የበለጠ የሚያከብር አዲስ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስምምነት” እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።
ጉባኤው ወደ 40 የሚጠጉ የሀገር መሪዎችን ያካተተ እና የዓለምን የኢኮኖሚ ስርዓት ለመቅረጽ ያለመ ሲሆን ነው።
በተለይም የአየር ንብረት ቀውስን ለመቋቋም እና ከድህነት ለመውጣት በትሪሊዮን የሚቆጠር ዶላር ያስፈልጋል ተብሏል።