ክርስቲያን ታቢራ ለፈረንሳይ ፕሬዘዳንትነት እንደሚወዳደሩ አስታወቁ
እጩ ፕሬዘዳንቷ በቀድሞው የሀገሪቱ ፕሬዘዳንት ፍራንሷ ሆላንድ ጊዜ የፍተህ ሚኒስትር ነበሩ
ነጋዴዋ ጂያን ሉክ ሜሌንሽን የፈረንሳይ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫን ሊያሽንፉ እንደሚችሉ ተገምቷል
ክርስቲያን ታቢራ ለፈረንሳይ ፕሬዘዳንትነት እንደሚወዳደሩ አስታወቁ፡፡
ፈረንሳውያን የፊታችን ሚያዝያ ላይ ፕሬዘዳንታቸውን እንደሚመርጡ የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን ገልጿል፡፡
በዚህ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ላይ የሚወዳደሩ ዕጩ ፕሬዘዳንቶች ራሳሳውን ለመራጩ ህዝብ በማሳወቅ ላይ ሲሆኑ ክርስቲያን ሳቢራ እንዲመረጡ በይፋ ቅስቀሳቸውን ዛሬ እንደጀመሩ ፍራንስ 24 ዘግቧል፡፡
ከአራት ወራት በኋላ እንደሚካሄድ በሚጠበቀው የፈረንሳይ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ እስካሁን ስድስት እጩዎች የቀረቡ ሲሆን ክርስቲያን ታቢራ ሰባተኛዋ እጩ ተወዳዳሪ መሆናቸውን ዘገባው አክሏል፡፡
የ69 ዓመቷ የህግ ባለሙያ ክርስቲያን ታቡራ የወቅቱ የፈረንሳይ ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን መንግስት ላይ ውሳኔዎች ከላይ ወደታች ናቸው፣ አሳታፊ አይደሉም እና ማህበራዊ ፍትህ ተጓድሏል በማለት በመተቸት ይታወቃሉ፡፤
ስልጣንን የአገሪቱ ከወዲሁ በፈረንጆቹ ከ2012 እስከ 2017 ዓመት ድረስ የፈረንሳይ ፍትህ ሚኒስትር የነበሩት ክርስቲያን ታቢራ በዕጩነት ቀረ፡፡
በሊዮን ከተማ ለደጋፊዎቻቸው ባሰሙት ንግግራቸው በሚያዚያው ፕሬዘዳናታዊ ምርጫ ከተመረጡ የሰራተኞችን ክፍያ አሳድጋለሁ፣የትምህርት ቤቶችን ጥራት አሳድጋለሁ፣የጤና ተቋማትን አገልግሎት ጥራት አሻሽላለሁ እና ለአካባቢ ጥበቃ ልዩ ትኩረት የሚሰጥ መንግስት እመሰርታለሁ ብለዋል፡፡
ክርስቲያን ታቢራ ከዚህ በፊት የባሪያ ንግዶች በሰብዓዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል መሆን አለበት በሚል በፈረንጆቹ 2013 ዓመት ባሳተሙት መጽሃፍ ላይ አስፍረዋል፡፡
የንግድ ሰው መሆናቸው የሚነገርላቸው ጂያን ሉክ ሜሌንሽን የፈረንሳይ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ እጩ ተወዳዳሪዎች መካከል በመራጮች ጥሩ ድጋፍ እንዳላቸው ይገመታል፡፡
የፓሪስ ከተማ ከንቲባ የሆኑት አኔ ሂዳልጎ እንዲሁም ከዚህ በፊት ምርጫውን እንደሚያሽንፉ ትልቅ ግምት ተሰጥቷቸው የነበሩት ግራ ዘመሟ ማሪን ለፐን በዘንድሮው ምርጫ ላይ ብርቱ ፉክክር እንደሚያደርጉ ተጠብቋል፡፡