የቀድሞው የሲአይኤ ሰራተኛ የ40 አመታት እስር ተፈረደበት
አቃቤ ህግ በግለሰቡ ላይ የእድሜ ልክ እስራት እንዲፈረድበት ቢጠይቅም፣ ፍርድቤቱ አልተቀበለውም ተብሏል
ጆሹዋ ስቹልቴ የተባለው ይህ ግለሰብ ሚስጥራዊ መረጃ ዊኪሊክስ ለተባለው ኤጀንሲ ሰጥቷል በሚል የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላልፎበት ነበር
የቀድሞ የሲአይኤ ሰራተኛ የ40 አመታት እስር ተፈረደበት።
ሚስጥራዊ መረጃዎችን በመስረቅ እና በህጻናት ወሲባዊ ፊልሞች ጥፋተኛ የተባለው የቀድሞው የሴንትራል ኢንተሊጀንስ ኤጀንሲ(ሲአይኤ) ሰራተኛ የ40 አመት እስር እንደተፈረደበት ሮይተርስ ዘግቧል።
የአሜሪካ ፌደራል አቃቤ ህግ ባወጣው መግለጫ ግለሰቡ የ40 አመት እስር የተላለፈበት "ስላላ በማድረግ፣ ኮምፒዩተር በመጥለፍ፣ ለኤፍቢአይ ሀሰተኛ መረጃ በመስጠት እና የህጻናት ወሲባዊ ፊልም በመቀበል" ነው ብሏል።
አቃቤ ህግ በግለሰቡ ላይ የእድሜ ልክ እስራት እንዲፈረድበት ቢጠይቅም፣ ፍርድቤቱ አልተቀበለውም ተብሏል።
ጆሹዋ ስቹልቴ የተባለው ይህ ግለሰብ ሚስጥራዊ መረጃ ዊኪሊክስ ለተባለው ኤጀንሲ ከሰጠ በኋላ "በስላላ፣ ኮምፒዩተር በመጥለፍ፣ ለአፍቢአይ ሀሰተኛ መረጃ በመስጠት" ባለፈው ሀምሌ ወር የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላልፎበት ነበር።
ባለፈው ነሀሴ ወር ጉዳዮን ያዩት ዳኛ ጥፋተኝነቱን አጽንተውታል።
ዊኪሊክስ በፈረንጆቹ 2017 የአሜሪካ የስለላ ድርጅት ሲአይኤ የውጭ መንግስታትን፣ አክራሪ የተባሉ ኃይሎችን እና የሌሎችን የኮምፒዩተር ኔቶርኮችን በመጥለፍ እንዴት እንደሚሰልል ይፋ ማድረግ መጀመሩ ይታወሳል።
አቃቤ ህግ የስቹሌትን ተግባር "በሲአይኤ ታሪካ ግዙፍ የሚባል የመረጃ ጥሰት" እና በዚህም ግዙፍ የሚባል ፍቃድ የሌላው ሚስጥራዊ መረጃ ተላልፎ መሰጠቱን ገልጿል።
አቃቤ ህግ አክሎም በስቹልት መኖሪያ ቤት በሺዎች የሚቆጠሩ የህጻናት ወሲባዊ ምስሎች እና ቪዲዮዎች አግኝቻለሁ ብሏል።