የአሜሪካው የስለዳ ድርጅት ሲአይኤ ሁሉንም ሰራተኞቹን ሊያሰናብት ነው
ተቋሙ የስራ መልቀቂያ ለሚያስገቡ ሰራተኞቹ የስምንት ወራት ደመወዝ እከፍላለሁ ብሏል
ሲአይኤ በአሜሪካ ህግን ተከትለው ከማይፈጸሙ ጥፋቶች ጀርባ እጁ አለበት የሚል ቅሬታ ቀርቦበታል
የአሜሪካው የስለዳ ድርጅት ሲአይኤ ሁሉንም ሰራተኞቹን ሊያሰናብት ነው፡፡
ከአንድ ወር በፊት 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሆነው ወደ ነጩ ቤተ መንግስት ከመጡ በኋላ በርካታ ለውጦት እየታዩ ነው፡፡
የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ውሳኔዎች ከአሜሪካ ባለፈ በዓለም ፖለቲካ እና ዲፕሎማሲ ላይ ተጽዕኖ በመፍጠር ላይ ሲሆኑ አሁን ደግሞ ማዕከላዊ የስለላ ድርጅቱ ሲአይኤ ሆኗል፡፡
በአሜሪካ በተለምዶ ዲፕ ስቴት ወይም ህግን የማይከተል ተጽዕኖ ፈጣሪ ቡድን በርካታ ጥፋቶችን የአሜሪካው የስለዳ ድርጅት ሲአይኤ ሁሉንም ሰራተኞቹን ሊያሰናብት ነው፡፡
ዶናልድ ትራምፕ ከአንድ ወር በፊት 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ወደ ነጩ ቤተ መንግስት ከመጡ በኋላ በርካታ ለውጦት እየታዩ ነው፡፡
የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ውሳኔዎች ከአሜሪካ ባለፈ በዓለም ፖለቲካ እና ዲፕሎማሲ ላይ ተጽዕኖ በመፍጠር ላይ ሲሆኑ አሁን ደግሞ ማዕከላዊ የስለላ ድርጅቱ ሲአይኤ ሆኗል፡፡
በአሜሪካ በተለምዶ ዲፕ ስቴት ወይም ህግን የማይከተል ተጽዕኖ ፈጣሪ ቡድን በርካታ ጥፋቶችን ሲፈጸም ሲአይኤ ዝም ብሏል የሚል ክስ በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀርቦበታል፡፡
አዲሱ የሲአይኤ ሃላፊም ቢሮውን በተረከቡ በጥቂት ቀናት ውስጥ ሰራተኞች ስራ እንዲለቁ የጠየቁ ሲሆን የስራ መልቀቂያ ለሚያስገቡ ሰራተኞች የስምንት ወር ደመወዝ እንደሚከፈላቸውም ተናግረዋል ተብሏል፡፡
እንደ ሲኤንኤን ዘገባ ከሆነ ሰራተኞች ሁሉ ስራ እንዲለቁ የሚበረታቱ ሲሆን በተቀመጠላቸው ቀነ ገደብ ውስጥ መልቀቂያ ለሚያስገቡ ሰራተኞች እስከ መጪው መስከረም ወር ድረስ ያለው ደመወዛቸው ይከፈላቸዋል፡፡
በተሰጣቸው ቀነ ገደብ ውስጥ የስራ መልቀቂያ የማያስገቡ ሰራተኞች ከስራ የመሰናበት እጣ ሊደርስባቸው እንደሚችልም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
ይሁንና ከፍተኛ እና ጥብቅ የሀገር ሚስጥሮችን የያዙ ሰራተኞች እጣ ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል በይፋ አልተጠቀሰም፡፡
ዶናልድ ትራምፕ ወደ ስልጣን ከመጡ ጊዜ ጀምሮ በተለይም ቁልፍ እና ዋና በሚባሉ የስራ ቦታዎች ላይ ሲሰሩ የነበሩ ሰራተኞችን ስራ ከማስለቀቅ ባለፈ ሰራተኞችን በስፋት የማሰናበት ውሳኔ ሲወሰን ሲአይኤ የመጀመሪያው ነው ተብሏል፡፡
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና መንግስታቸው ሲአይኤን በአዲስ ሀይል የማደራጀት እቅድ እንዳላቸውም ተገልጿል፡፡