ግጭቱ የተከሰተው የፕሬዝዳንት ኢሳያስ ደጋፊዎች እና ተቃዋሚዎች መካከል ነው ተብሏል
በጀርመን በሚኖሩ ኤርትራዊያን መካከል ግጭት መከሰቱ ተገለጸ፡፡
በጀርመን የሚኖሩ ኤርትራዊያን በተደጋጋሚ ከሀገሪቱ ፖሊሶች ጋር ግጭት ውስጥ ሲገቡ ይስተዋላል፡፡
በጀርመኗ ጌሰን ከተማ የኤርትራ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ደጋፊዎች እንደሆኑ የተጠረጠሩ ኤርትራዊያን ባህላዊ ዝግጅት ማዘጋጀታቸውን ዶቸቪሌ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ ይህን ባህላዊ ዝግጅት እንዲከናወን ያልፈለጉ ኤርትራዊያን ደግሞ ዝግጅቱን ለማወክ ወደ ስፍራው በማቅናታቸው ግጭቱ ተከስቷል፡፡
የጀርመን ፖሊስም ሁኔታውን ለመቆጣጠር ከ8 ሺህ በላይ አባላቱን ማሰማራቱን አስታውቋል፡፡
የኤርትራ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ደጋፊ እና ተቃዋሚ ናቸው በተባሉ ትውልደ ኤርትራዊያን መካከል የተፈጠረውን ግጭት ለመቆጣጠር ከተሰማሩ የጀርመን ፖሊሶች መካከልም 26 ፖሊሶች መጎዳታቸው ተገልጿል፡፡
ኤርትራዊያኑ በምስራቅ ጀርመን የተዘጋጀውን ባህላዊ ዝግጅት ለማወክ በሚገባ ተዘጋጅተው እንደ ነበር የተገለጸ ሲሆን ፊት እና አይን ላይ የሚረጩ የሚያቃጥሉ ቁሳቁሶችን ሳይቀር ይዘው ነበር ተብሏል፡፡
የጀርመን ፖሊስ 60 ተጠርጣሪዎችን በህግ ቁጥጥር ስር ማዋሉን ሲገልጽ ኤርትራዊያን እንደዚህ አይነት መሰል ግጭቶችን ሲያደርጉ የአሁኑ የመጀመሪያቸው እንዳልሆነም ተገልጿል፡፡
የጊዜ ከተማ ይህ የኤርትራ ባህላዊ ፌስቲቫል እንዳይካሄድ አግዳ የነበረ ቢሆንም ፍርድ ቤት ፌስቲቫሉ ሊታገድ የሚችልበት ምንም አይነት አስገዳጅ ምክንያት የለም በሚል እግዱን ከልክሏል ተብሏል፡፡