ለአየር ንብረት ጥበቃ ስራዎች 24 ትሪሊየን ዶላር ያስፈልጋል - ዶክተር ማህሙድ ሞሄልዲን
ዶክተር ሞሄልዲን በግብጽ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ በሰሯቸው ስራዎች ተመድ እውቅና ሰጥቷቸዋል
በአለማቀፍ የልማትና ፋይናንስ ተቋማት በኩል 1 ትሪሊየን ዶላር ለታዳጊ ሀገራት መቅረብ እንዳለበትም ተናግረዋል
የአየር ንብረትጥበቃ ስራዎችን በፍጥነት ለማነቃቃት በማደግ ላይ ለሚገኙ እና ድሃ ሀገራት በጥቂቱ 2 ነጥብ 4 ትሪሊየን ዶላር ፈንድ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ።
ለ30 አመታት በአለማቀፍ የፋይናንስ ተቋማት የሰሩት የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ዶክተር ማህሙድ ሞሄልዲን እንደገለጹት፥ የአለም የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ በሁሉም ዘርፎች የፋይናንስ አቅርቦቱ በእጥፍ ሊያድግ ይገባል።
የአየር ንብረት ለውጥን ለሚገቱ ስራዎች ለታዳጊ ሀገራት የሚቀርበው ፋይናንስ 2 ነጥብ 4 ትሪሊየን ዶላር መድረስ እንዳለበትም አሳስበዋል።
ከዚህ ውስጥ 1 ትሪሊየን ዶላሩ በአለማቀፍ የልማትና የፋይናንስ ተቋማት በኩል መቅረብ እንዳለበት በመጥቀስ።
ዶክተር ሞሄልዲን ለኤምሬትሱ የዜና ወኪል ዋም እንደተናገሩት፥ በዱባይ በሚካሄደው የአለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ የፋይናንስ ጉዳይ ትልቅ ትኩረት ይሰጠዋል።
የመንግስታቱ ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ27) ባለፈው አመት በግብጽ ሲካሄድ የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳት እና ኪሳራን የሚያካክስ ድጋፍ እንዲደረግ መስማማታቸው ይታወሳል።
ሀገራት ስለሚደረገው ድጋፍ የሚደራደርና 28 አባላት ያሉት ኮሚቴ ማዋቀራቸውም አይዘነጋም።
ይህ ኮሚቴ ለአንድ አመት በአቡዳቢ ሲያደርገው የነበረውን ድርድር ያጠናቀቀ ሲሆን፥ ጊዜያዊ ስምምነት ላይ ደርሷል።
ይሄው ጊዜያዊ ስምምነት በኮፕ28 ጉባኤ ለመሪዎች ቀርቦ ንግግር እንደሚደረግበት ዶክተር ሞሄልዲን ገልጸዋል።
ዶክተር ማህሙድ ሞሄልዲን በግብጽ ለአየር ንብረት ለውጥ መከላከል የሚውል የፋይናንስ አቅርቦትን በማመቻቸት እና በሌሎች ተያያዥ ስራዎች አርአያ የሚሆን ተግባር በመፈጸም በመንግስታቱ ድርጅት እውቅና ተሰጥቷቸዋል።