አፍሪካ ለኮፕ 28 ጉባዔ ስኬት ሙሉ ድጋፍ እሰጣለሁ አለች
የአፍሪካ የአየር ንብረት ተደራዳሪዎች ቡድን የኮፕ 28 ፕሬዝዳንት ራዕይን እንደሚደግፍ አስታወቀ
ቡድኑ በግብጽ በተካሄደው ጉባኤ የተገኙ ውጤቶችን ቃኝቷል
የአፍሪካ የአየር ንብረት ተደራዳሪዎች ቡድን በአረብ ኢሚሬትስ ለሚካሄደው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 28) አዘጋጅ ሙሉ ድጋፍ እንደሚሰጥ ገልጿል።
ቡድኑ በሚቀጥለው ዓመት መጀመሪያ ላይ በዱባይ ለሚካሄደው ድርድር ስኬት ቁርጠኛ መሆኑን አስታውቋል።
የአህጉሪቱ የተደራዳሪዎች ቡድን ይህን ያለው በቦን የአየር ንብረት ድርድር ላይ በሰጠው መግለጫ ነው።
ቡድኑ 54 የአፍሪካ ሀገራትን በመወከል በሁሉም ይፋዊ የአየር ንብረት ጉዳዮች ላይ የሚደራደር ሲሆን የሀገራቱን ፍላጎት የሚገልጹ የጋራ ጥያቄዎችን ያቀርባል።
የቡድኑን አጀንዳ፣ እቅዱን እና የድርድር ሀሳቦችን ቅጂ የተመለከተው የአል ዐይን ኒውስ ለኮፕ 28 ፕሬዝዳንት ድጋፍ መስጠቱን አረጋግጧል።
ቡድኑ በግብጽ ሻርም ኤል ሼክ በተካሄደው ያለፈው የአየር ንብረት ጉባኤ ታሪካዊ ውጤቶችን በተለይም ለኪሳራ እና ለጉዳት የሚደረጉ የፋይናንስ ዝግጅቶችን ፣የፓሪስን ስምምነት አተገባበር ለማስቀጠል ያለውን መርሃ ግብር እና የሽግግር መንገዶችን ቃኝቷል።
የአፍሪካ ቡድን የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የአየር ንብረት ለውጥ ልዩ መልዕክተኛ እና የኮፕ 28 ጉባኤ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሱልጣን ቢን አህመድ አል ጃብር ራዕይን እንደሚደግፍና ስምምነት እንዳለው አስታውቋል።
ድጋፉ የኮፕ 28 ቃል ኪዳኖችን በጥሩ ሁኔታ ማከናወን፣ ለጉባኤው ስኬት ዓላማዎችን እና ቀደምት የትግበራ ተስፋዎችን የሚያካትት ነው ተብሏል።
የአፍሪካ ቡድን የኮፕ 28 ትልቅ ውጤት እንዲያመጣ እና የፓሪሱን ስምምነት የሚፈጽሙ የውሳኔ ሃሳብ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት መላመድ እና መቋቋም እንዲያመጣ መሰራት እንዳለበት ጠይቋል።