ኮፕ 28 ልቀትን በመቀነስ ረገድ ትልቅ ለውጥ ያመጣል-የቦን የአየር ንብረት ማዕከል መስራች
ሄንዝ ስቱርም የአየር ንብረት ለውጥን ለመቅረፍ ሁለንተናዊ ስራ ቁልፍ ነው ብለዋል
የኮፕ 28 ጉባኤ አስፈላጊና እንቅስቃሴዎችን ወደፊት የሚያራምድ መሆኑን ገልጸዋል
ለዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ፖሊሲ ጠንካራ ጥሪ የሚያቀርበው የቦን የአየር ንብረት ማዕከል መስራችና ተመራማሪ ኢንጂነር ሄንዝ ስቱርም በተቋማት መካከል ትስስርን መፍጠር አስፈላጊ ነው ብለዋል።
ለአየር ንብረት ጥበቃ የሃይድሮጂን አጠቃቀምን ለማበረታታት በቦን የአየር ንብረት ፕሮጀክት ፣ በተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ሴክሬታሪያት እና በሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች መካከል ግንኙነትን መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል።
በአለም አቀፍ የአየር ንብረት ጥበቃ ጉዳዮች ላይ ተሟጋች በመሆን ለዓመታት የሰሩት ሄንዝ ስቶርም በአሁኑ ጊዜ የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ሴክሬታሪያት እና ለአንዳንድ የአፍሪካ እና የአረብ ሀገራት አማካሪ ናቸው።
የአየር ንብረት ለውጥን ለመቅረፍ ሁለንተናዊ ስራ ቁልፍ ነው ብለዋል።
ለ15 ዓመታት የሰራው የቦን የአየር ንብረት ማዕከልን ፍልስፍና ጠቅለል አድርገው ሲገልጹ፤ "ሃይድሮጂን በአየር ንብረት ጥበቃ እና በንጹህ የኃይል አቅርቦት ላይ ያለውን ስኬት የሚወስነው የግለሰብ ቴክኖሎጂ ወይም ተነሳሽነት ሳይሆን እንደ ማህበረሰብ የሚወሰድ እርምጃ ነው" ብለዋል።
የአረብ ሀገራት በተለይም አረብ ኤምሬትስ ኢኮኖሚያዊ እና አእምሯዊ አቅም እና ከአየር ንብረት እና ኃይል ሽግግር ጋር በተያያዙ ፕሮጀክቶች ላይ ፈጠራን ማበረታታት ፈጣን ለውጥ ለመፍጠር ቁልፍ ናቸው ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል።
ይህም ለአረብ ቀጠና ልዩ የጂኦፖለቲካዊ ሁኔታን በማጉላት እኩልነት እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመፍታት ሚና አለው ብለዋል።
አማካሪው በሚቀጥለው ህዳር በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የሚካሄደውን የኮፕ 28 የአየር ንብረት ጉባኤ የዓለም ሙቀት መጨመርን የሚያስከትሉ ልቀቶችን ለመቀነስ ትልቅ ለውጥ ያመጣል የሚል እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል።
የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ሴክሬታሪያት አማካሪ እና የቦን የአየር ንብረት ቴክኖሎጂ ማዕከል መስራች ለአል አይን የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና የሳዑዲ አረቢያን ቁርጠኝነት አጉልተዋል።
የአየር ንብረት ጥበቃ፣ የሃይድሮጅን እና የሙቀት አማቂ ጋዞችን ለመቀነስ ተነሳሽነት እና ጥረቶች ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ከሳዑዲ አረቢያ የሚመነጩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ስለሆነም የኮፕ 28 ጉባኤ አስፈላጊ እና ወቅታዊ ያሉት ኢንጂነር ሄንዝ ስቱርም እንቅስቃሴዎችን ወደፊት የሚያራምድ ነው ብለዋል።
የዱባዩ ጉባኤ በጣም ጠቃሚ እድልን ይወክላል ያሉም ሲሆን፤ ምክንያቱም የአረብ ክልል በዚህ ጊዜ በዓለም አቀፍ ግቦች ትግበራ ላይ በንቃት ለመሳተፍ ፣ ልቀትን ለመቀነስ ቃል በመግባት አስፈላጊ ነው ሲሉም አክለዋል።