በየሀገሩ እየተካሄዱ ያሉ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቃወሙ ሰላማዊ ሰልፎች ለውጥ ያመጡ ይሆን?
መንግስታት ለአየር ንብረት ለውጥ ትኩረት እንዲሰጡ የሚጠይቁ ሰላማዊ ሰልፎች እና ቁጣዎች ቀጥለዋል
የአየር ንብረት ለውጥ እውነተኛ አይደለም የሚል አመለካከት ያላቸው ዜጎች አሁንም ከፍተኛ ነው ተብሏል
በየሀገሩ እየተካሄዱ ያሉ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቃወሙ ሰላማዊ ሰልፎች ለውጥ ያመጡ ይሆን?
የአየር ንብረት ለውጥ እና እያስከተላቸው ያለው ጉዳት እንደቀጠለ ሲሆን ሀገራት እና ተቋማት ተገቢውን ትኩረት እንዳልሰጡ ይገለጻል።
ይህን ተከትሎ በተለያዩ ሀገራት ያሉ ዜጎች መንግስታት ለአየር ንብረት ለውጥ ትኩረት እንዲሰጡ በተለያየ መንገድ በመጠየቅ ላይ ናቸው።
የኖርዌይ ተመራማሪዎች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እየተደረጉ ባሉ ሰላማዊ ሰልፎች ዙሪያ ባደረጉት ጥናት ተሳታፊዎች ንዴት እንደሚሰማቸው ተናግረዋል።
የበርገን ዩንቨርስቲ ሶስት ተመራማሪዎች ባደረጉት ጥናት ከሁለት ሺህ በላይ ሰዎች በጥናቱ ተሳትፈዋል።
ከተሳታፊዎቹ መካከልም አብዛኞቹ መንግስታት ለአየር ንብረት ለውጥ ትኩረት አለመስጠታቸው እንደሚያናድዳቸው ተናግረዋል ።
በጥናቱ ከተሳተፉ ከሁለት ሺህ በላይ መላሾች ውስጥ ከግማሽ በላይ ያህሉ የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ እንደሚያሳስባቸው ተናግረዋል።
የሰው ልጆች ለአየር ንብረት ለውጥ መከሰት እና የከፋ ጉዳት ዋነኛ ተጠያቂ እንደሆኑም የጥናቱ ተሳታፊዎች መናገራቸው ተገልጿል።
ከዚህ በፊት የተሰራ ተመሳሳይ ጥናት የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳቶች እንዲቀንሱ አልያም እንዲቆም የሚያደርጉ ቴክኖሎጂዎች ይተገበራሉ ብለው ያስቡ እንደነበር ተገልጿል።
ይሁንና የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳቶችን ሊያስቀሩ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን ከመተግበር አንጻር የተሰራው ስራ ዝቅተኛ ነው ተብሏል።