እንደ ዓለም ባንክ መረጃ ከሆነ 43 በመቶ የዓለማችን ህዝብ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ለግጭት የበለጠ ተጋላጭ ይሆናሉ
የአየር ንብረት ለውጥ ለግጭት እና ጦርነት ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ተገለጸ።
የዓለማችን ሁለቱ የገንዘብ ተቋማት አይኤምኤፍ እና ዓለም ባንክ የአየር ንብረት ለውጥ በሀገራት ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት አስመልክቶ ሪፖርታቸውን ይፋ አድርገዋል።
በዚህ ሪፖርት መሰረትም የአየር ንብረት ለውጥ ለግጭቶች እና ጦርነት ምክንያት ሊሆን ይችላል ተብሏል።
እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥ በዚሁ ከቀጠለ ለረሀብ፣ አስከፊ ድህነት እና መፈናቀሎችን እንደሚያስከትልም ተገልጿል።
በፈረንጆቹ 2060 ላይ ከፍተኛ ሙቀት በሚመዘገብባቸው ሀገራት በግጭቶች ምክንያት የሚከሰት ሞት መጠን በ8 ነጥብ 5 በመቶ ጭማሪ እንደሚያሳይ ተገልጿል።
39 የአየር ንብረት ለውጥ የሚመዘገብባቸው የዓለማችን ሀገራት ካለው ጠቅላላ የድሀ ዜጎች ቁጥር የ43 በመቶ ድርሻን ይይዛሉም ተብሏል።
አፍሪካ ከሌሎች አህጉራት ጋር ሲነጻጸር የበለጠ ተጎጂ ይሆናሉ የተባለ ሲሆን በ2060 50 ሚሊዮን ዜጎችም ወደ አስከፊ ድህነት ውስጥ ሊገቡ እንደሚችሉ ተጠቅሷል።
የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳት ባልተረጋጉ እና የጸጥታ ችግሮች ባሉባቸው ሀገራት ላይ የከፋ እንደሚሆን የሁለቱ ተቋማት ሪፖርት ያስረዳል።
በአፍሪካ ቀንድ የአየር ንብረት ለውጥ እና ግጭቶች የሀገራቱን አለመረጋጋት እያባባሱት እንደሆነም ተገልጿል።