በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ዓለም በየሰአቱ 16 ሚሊዮን ዶላር እየከሰረች ነው- ጥናት
ከፈረንጆቹ 2000-2019 በከባድ የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት 143 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ያለው ንብረት ወድሟል
ባለፉት አስርት አመታት ጎርፍ፣ አውሎ ንፋስ እና ድርቅ ለብዙ ሰዎች ሞት ምክንያት ሆኗል፤ በሰፊ ቦታ ላይ የነበረ ንብረትንም አውድሟል
የአየር ንብርት ለውጥ ዓለም በየሰአቱ 16 ሚሊዮን ዶላር እያከሰራት መሆኑን ጥናት አመለከተ።
ባለፉት አስርት አመታት ጎሮፍ፣ አውሎ ንፋስ እና ድርቅ ለብዙ ሰዎች ምክንያት ሆኗል፤ በሰፊ ቦታ ላይ የነበረ ንብረትንም አውድሟል።
ይህ የተከሰተው የዓለም የሙቀት መጠን በመጨመሩ እና አደጋዎቹ በተደጋጋሚ እንዲከሰቱ በማድረጉ ነው። ይህ ጥናት በሰው ልጅ አማካኝነት በሚከሰተው የዓለም የሙቀት መጠን መጨመር ዓለም ምን ያህል ታጣለች የሚለውን ለመጀመሪያ ጊዜ አስልቷል።
ባለፉት 20 አመታት እንደ አውሎንፋስ፣ጎርፍ እና የሙቀት ሞገድን የመሳሰሉ የዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ክስተቶች 2.8 ትሪሊየን ጉዳት ማድረሳቸውም ጥናቱ ገልጿል።
ከፈረንጆቹ 2000-2019 በከባድ የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት 143 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ያለው ንብረት ወድሟል።