የአየር ንብረት ትብብር ጎልቶ ያወጣው የአረብ ኤምሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትርና ባርባዶስ ጠ/ሚንስትር ጋር ውይይት
በአየር ንብረትና በታዳሽ ኃይል አቅምን ለማጎልበት ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል
በምጣኔ-ሀብተሰ፣ ቱሪዝምና ንግድ ያለውን የሁለትዮሽ ትብብር ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል
የአረብ ኤምሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሼክ አብዱላህ ቢን ዛይድ አል ናህያን እና የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ አሞር ሞተሊ በሁለቱ ሀገራት መካከል ስላለው ትብብር መክረዋል።
ሀገራቱ በሁሉም መስኮች በተለይም በአየር ንብረት እና በታዳሽ ኃይል አቅምን ለማጎልበት ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።
ይህ የተባለው የአረብ ኤምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በቤርቤዶስ ሪፐብሊክ የስራ ጉብኝት ሲያደርጉ ነው።
- አረብ ኤምሬትስ ለአፍሪካ የ4.5 ቢሊዮን ዶላር ታዳሽ ኃይል ልማት አጋርነት ይፋ አደረገች
- አረብ ኤምሬትስ ተጽዕኖ ፈጣሪ ጉባኤ ለማሰናዳት ትፈልጋለች- የ"ኮፕ 28" ቢሮ ዋና ዳይሬክተር
ሼክ አብዱላህ ቢን ዛይድ አል ናህያን እና የቤርቤዶስ ጠቅላይ ሚንስትር ሁለቱ ሀገራት ዘላቂ እድገትን ለማስመዝገብ የሚያደርጉትን ጥረት ለማገዝ በተለያዩ ዘርፎች ላይ መክረዋል።
መሪዎቹ በምጣኔ-ሀብተሰ፣ ቱሪዝም እና ንግድ ያለውን የሁለትዮሽ ትብብር ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።
ሼክ አብዱላህ ቢን ዛይድ አል ናህያን 28ተኛውን የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን (ኮፕ 28) ለማስተናገድ እየተደረገ ስላለው ዝግጅት ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትሯ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
እንዲሁም የዝግጅቱ አጀንዳ እና የጉባኤው ፕሬዝዳንት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የትኩረት አቅጣጫዎችን በተመለከተ ለጠቅላይ ሚንስትሯ አብራርተዋል።
በተለይም የአየር ንብረት እንቅስቃሴን ለመደገፍና ፍትሃዊ የኃይል ሽግግርን ማምጣት የፋይናንስ አቅርቦትን ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረትን ገልጸዋል።