የአየር ንብረት ለውጥ የቢራ ጣዕምን ሊቀይር እንደሚችል ተገለጸ
የዓለም ቢራ ጣዕም ጥራት በየጊዜው እየቀነሰ ነው ተብሏል
በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የቢራ ጣዕም እስከ 35 በመቶ ሊቀንስ እንደሚችል ተገልጿል
የአየር ንብረት ለውጥ የቢራ ጣዕምን ሊቀይር እንደሚችል ተገለጸ፡፡
የዓለማችን ሀብታሙ አህጉር የሚባለው አውሮፓ ብዛት ያለው አልኮል የሚጠጣበት አህጉርም ነው፡፡
ተመራማሪዎች እንዳሉት የቢራ ጣዕም ጥራት በየጊዜው እየቀነሰ መምጣቱን ገልጸዋል፡፡ እንደ ተመራማሪዎቹ ገለጻ ለቢራ ጣዕም መቀየር የአየር ንብረት ለውጥ ዋነኛው ምክንያት ነው፡፡
ለቢራ ጣዕም አስፈላጊ የተባሉ ንጥረ ነገሮች ወይም ግብዓት በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እየተጎዱ መምጣታቸውንም ተመራማሪዎቹ ገልጸዋል፡፡
ስካይ ኒውስ የብሪታንያ እና ሌሎች የአውሮፓ ሀገራት ተመራማሪዎችን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በሚደርሱ ጉዳቶች ከጣዕም ጥራት መጓደል በተጨማሪ የዋጋ ጭማሪንም አስከትሏል፡፡
አሜሪካ ከሻወር እና ኩሽና ውሀ ፍሳሾች ቢራ ጠመቀች
በኔቸር ጆርናል ኮሙንኬሽን ላይ የወጣው ይህ ጥናት እና ምርምር የቢራ ጣዕም እስከ 35 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል፡፡
ብሪታንያ፣ ስሎቬኒያ፣ ፖርቹጋል እና ስፔን በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ከፍተኛ የቢራ ጣዕም ለውጥ የታየባቸው ሀገራት ተብለዋል፡፡
በመሆኑም ቢራን ለመጥመቅ ግብዓት የሚያመርቱ አርሶ አደሮች እና ጠማቂዎች ራሳቸውን ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ማስማማት የሚያስችሉ ስራዎችን እንዲሰሩ ጥናቱ አሳስቧል፡፡
ደቡብ እና መካከለኛው የአውሮፓ ሀገራት ችግሩ በስፋት የተከሰተባቸው ሀገራት ሲሆኑ ባሳለፍነው ክረምት ወራት ውስጥ ግማሽ የአውሮፓ ሀገራት ከፍተኛ ሙቀት አስተናግደው እንደነበር ተገልጿል፡፡