የጃፓኑ ኦሪዮን ቢራ ፋብሪካ ወደ ባህር ፈሰሰ
ከቢራ ፋብሪካው የወጣው ፈሳሽ ሰማያዊ የነበረውን ባህር ወደ ቀይነት ቀይሮታል
ኦሪዮን ቢራ ፋብሪካ ለተፈጠረው ክስተት ይቅርታ ጠይቋል
የጃፓኑ ኦሪዮን ቢራ ፋብሪካ ወደ ባህር ፈሰሰ።
የጃፓኑ ናጎ ባህር ባልተለመደ ሁኔታ መልኩን ወደ ቀይነት ሲቀይር ብዙዎችን አስገርሟል።
በባህሩ መልክ መቀየር የተገረሙ ጃፓናዊያን ወንዙን ለመጎብኘት ወደ ስፍራው እየተጓዙ ነበርም ተብሏል።
ቆይቶ በወጣ መረጃ ግን የባህሩ መልክ ወደ ቀይነት የተቀየረው በሀገሪቱ ታዋቂ የሆነው ኦሪዮን ቢራ መፍሰሱን ተከትሎ ነው ሲል ሲኤንኤን ዘግቧል።
ፋብሪካው እንዳስታወቀው ክስተቱ የተፈጠረው እና የቢራ መልክ መቀየሪያ ግሊኮል የተሰኘው ኬሚካል ከቅዝቃዜ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ ችግር ነው ብሏል።
ለባህሩ መበከል ምክንያት በመሆኑ ይቅርታ የጠየቀው ኦሪዮን ቢራ ፋብሪካ መሰል ችግር ዳግም እንደማይከሰት አስታውቋል።
የአካባቢው አስተዳዳሪዎች በበኩላቸው ከቢራ ፋብሪካው ሰርጎ የወጣው በካይ ቀለም በአካባቢው ነዋሪዎች እና በባህሩ ብዝሀ ህይወት ላይ የከፋ ጉዳት እንዳላደረሰ ተናግረዋል።
ግሊኮል የተሰኘው ኬሚካል ከአልኮል ፋብሪካዎች ባለፈ የመዋቢያ አምራች ኢንዱስትሪዎች የምርቶቻቸውን ቀለም ለመቀያየር ይጠቀሙበታል።