አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ2ኛ ዙር ዝግጅት 28 ተጫዋቶችን ጠሩ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከየካቲት 1 እስከ 6 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ልምምድ እንደሚያደርግ ተገልጿል
ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች የካቲት 1 ቀን 2013 ዓ.ም ጽህፈት ቤት ሪፖርት እንዲያደርጉ ተብሏል
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ28 ተጫዋቶች ለ2ኛ ዙር የብሄራዊ ቡድኑ ዝግጅት ጥሪ ማድረጋቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡
ብሔራዊ ቡድኑ በቀጣይ ከማዳጋስካር እና ከኮትዲቯር ጋር ለሚያደርገው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎች የ2ኛ ዙር የልምምድ መርሃ ግብር ወጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከየካቲት 1 እስከ የካቲት 6 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ልምምድ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡ ዝግጅቱ የሚካሄደው በአፍሪከ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) አካዳሚ እንደሆነም ታውቋል፡፡ ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች የካቲት 1 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት ወሎ ሰፈር በሚገኘው የፌዴሬሽኑ ጽህፈት ቤት ሪፖርት እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርቧል፡፡
የተመረጡ ተጫዋቾች ስም ዝርዝር
1 ተክለማሪያም ሻንቆ
2 ጀማል ጣሰው
3 ፍሬው ጌታሁን
4 ፋሲል ገብረሚካኤል
5 አስቻለው ታመነ
6 ያሬድ ባየህ
7 ቶማስ ስምረቱ
8 ወንድሜነህ ደረጃ
9 ኤልያስ አታሮ
10 ረመዳን የሱፍ
11 አምሳሉ ጥላሁን
12 ሱሌማን ሀሚድ
13 አስራት ቱንጆ
14 ጋዲሳ መብራቴ
15 ሽመክት ጉግሳ
16 ታፈሰ ሰለሞን
17 መሱድ መሐመድ
18 አብዱከሪም ወርቁ
19 ሀብታሙ ተከስተ
20 ሀይደር ሸረፋ
21 ፍፁም አለሙ
22 ጌታነህ ከበደ
23 አቤል ያለው
24 አቡበክር ነስር
25 አማኑኤል ገብረሚካኤል
26 ሙጂብ ቃሲም
27 መስፍን ታፈሰ
28 አማኑኤል ዮሐንስ ናቸው።