የአሜሪካ የደህንነት ተቋም አደንዛዥ እጹ እንዴት እዛ ሊገኝ ቻለ የሚለው ላይ ምርመራ እያደረገ ነው
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የስራ ቦታ እና መኖሪያ በሆነው ዋይት ሃውስ ውስጥ ኮኬይን አደንዛዥ እጽ ተገኘ።
ባሳለፍነው እሁድ ምንነቱ ያልታወቀ ነጭ ጥቅል በቤተ መንግስቱ መገኘቱን ተከትሎ ሰራተኞች ዋይት ሃውስን እንዲለቁ ተደርጎ የነበረ ሲሆን፤ በተደረገው ምርመራም ኮኬይን ሆኖ መገኘቱን ቢቢሲ ዘግቧል።
ኮኬይን አደንዛዥ እጽ የተገኘው ለጉብኘት ክፍት ባልሆነ የስራ አካባቢ መሆኑንም የአሜሪካ የደህነንተ ተቋም (ሰክሪት ሰርቪስ) አስታውቋል።
ኮኬይኑ የተገኘበት የዋይት ሃውስ ሕንጻ አካል ‘ኦቫል ኦፊስ’ እና ‘ሲቹዌሽን ሩም’ ጨምሮ የፕሬዝዳንቱ ቢሮዎች የሚገኙበት ነው።
የዋይት ሃውስ ፕሬስ ሴክሬታሪ ካሪን ጄን ፒር ትናንት ምሽት በጉዳዩ ላይ በሰጡት መግለጫ፣ እጹ በተገኘበት ሰዓት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በቤተ መንግስት ውስጥ እንዳልነበሩ ህዝቡ ማወቅ አለበት ብለዋል።
ኮኬይን በዋይት ሃውስ መገኘቱን በማረጋገጥ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት የተቆጠቡት ቃል አቀባዩዋ፣ "ሁሉም ጥያቄዎች ወደ ሴክሪት ሰርሺስ ያመራሉ፣ ስፍራው ከፍተኛ የእጽ ማዘዋወሪያ ሆኖ ተገኝቷል" ብለዋል።
የአሜሪካ የደህንነት ተቋም (ሴክሬት ሰርሺስ) በዋይት ሃውስ በተገኘው ኮኬይን እጽ ዙሪያ ምርመራ ማካሄድ መጀመሩ ተመላክቷል።