ልዩልዩ
ኮኬን የጫነች መርከብ የማስቆም ትንቅንቅ
የአሜሪካ የባህር ጠባቂዎች በፓስፊክ ውቅያኖስ አደንዛዥ እጽ ከጫነች ባህር ሰርጓጅ መርከብ ጋር አስደናቂ ትንቅንቅ አድርገዋል
መርከቧ 232 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ 7 ሺህ 700 ኪሎግራም ኮኬን ጭና ነበር
የአሜሪካ የባህር ጠባቂዎች በፓስፊክ ውቅያኖስ አደንዛዥ እጽ ከጫነች ባህር ሰርጓጅ መርከብ ጋር አስደናቂ ትንቅንቅ አድርገዋል።
232 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ 17 ሺህ ፓውንድ ወይም 7 ሺህ 700 ኪሎግራም ኮኬይን የጫነችውን መርከብ ባህር ሰርጓጅ ብትሆንም ከእይታቸው ውጭ አልሆነችም።
የባህር ጠባቂዎቹ እየተከታተሉ ለማስቆም ያደረጉት ጥረት አልሳካ ሲልም፥ አንደኛው ዘሎ በመግባት የአደንዛዥ እጽ አዘዋዋሪውን በቁጥጥር ስር ሲውል የሚያሳይ ቪዲዮ የአሜሪካ ባህር ሃይል ተቋም ተለቋል።
አሜሪካ ኮኬን ከሀኪም ትዕዛዝ ውጭ ጥቅም ላይ እንዳይውል ብታግድም ከ5 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ሰዎች አደንዛዥ እጹን እንደሚጠቀሙ መረጃዎች ያሳያሉ።
የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ትዊተር: https://twitter.com/AlAinAmharic
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic