የአልዘዋሂሪ ግድያ ከኩየት ወረራ ክብረ በዓል ጋር መገጣጠሙ ቀጣናው አቋም እንዲይዝ እድል ይፈጥራል - አረብ ኢምሬትስ
የአልዘዋሂሪ ግድያ እና የኩየት ወረራ ክበረ በዓል ትምህርት ይሰጣሉ ብለዋል
ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ኦሳማ ቢላደንን ተክቶ የነበረውን የአልቃኢዳ መሪ አይማን አል ዘዋሂሪ መገደሉን አስታውቀዋል
የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝደንት አማካሪ ዶ/ር አኑዋር ጋርጋሽ የአይማን አል ዘዋሂሪ ግድያ እና ከኩየት ወረራ ክብረ በዓል ጋር መገጣጠሙ ቀጠናው በሽብርተኝነት ላይ አንድ አቋም እንዲይዝ እድል ይፈጥራል ብለዋል፡፡
ዶ/ር አንዋር ይህን ያሉት አይማን አል ዘዋሪ በአሜሪካ የአየር ጥቃት በአፍሪካኒስታን ውስጥ መገደሉን በማስመልከት በሰጡት አስተያየት ነው፡፡
አማካሪው በትዊተር ገጻቸው በጻፉት መልእክት የአል ቃኢዳው መሪ መገደል ከኩየት ወረራ መገጣጠሙ ቀጣናው በሽብርተኝነት፣ ብጽንፈኝነትና እና ግዴለሽ በሆነ ወታደራዊ እርምጀ ላይ አቋም እንዲይዝ እድል ይፈጥራል ብለዋል፡፡
ሁለቱ ክስተቶች ትምህርት ሰጥተዋል ብለዋል አማካሪው፡፡
የፕሬዝደንቱ የዲፕሎማቲክ አማካሪ በቀጣናው ያሉት ሀገራት በመተባበር ጸጥታ እና የጋራ ልማት እንደሚያረጋግጡ ተስፈቸውን ገልጸዋል፡፡ ዛሬ ኩየት በኢራን የተወረረችበት 32ኛ አመት እየተከበረ ነው፡፡
ፈረንጆቹ ነሐሴ 2 ቀን 1990 የሟቹ የኢራቅ ፕሬዝዳንት ሳዳም ሁሴን ወታደራዊ ጀብዱ ጀመሩ ፣ይህም በወቅቱ በአረብ ባህረ ሰላጤ ተቀያያሪ ክስተትን በመፍጠር ፣በአካባቢው ላይ ጥላ በመጣል ለከታታይ ክስተቶች በር ከፍቷል።
በአሜሪካ የአየር ጥቃት መገደሉን የገለጹት ፕሬዝደንት ባይደን በመገደሉ በሽብር ጥቃት ሰለባ የሆኑት አሜሪካውያን ፍትህ አግኝተዋል፡፡
የሽብር ቡድኑ መሪ፤ የአሜሪካ የስለላ ተቋም (ሲአይ ኤ) በፈጸመው የድሮን ተልዕኮ መገደሉን ጆ ባይደን አረጋግጠዋል። የቀድሞውን መሪ ኦሳማ ቢላደንን በመተካት አል ቃኢዳን ሲመራ የነበረው ትውልደ ግብፃዊው የተገደለው በአፍጋኒስታን ካቡል መሆኑንም ጆ ባይደን ተናግረዋል።
አይማን አል ዘዋሪ የተገደለው የሽብር ቡድኑን ቁልፍ መሪዎችን ኢላማ በማድረግ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት እንደሆነም ተገልጿል።
ሳኡዲ አረቢያ የአይማን አል ዘዋሪን ግድያ በበጎ መቀበሏን አስታውቃለች፡፡