ኮሊን ፖውል ከአውሮፓውያኑ 2001 እስከ 2005 የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤትን በበላይነት መርተዋል
የአሜሪካ የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኮሊን ፖውል ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን መገናኛ ብዙኃን እየዘገቡ ነው።
ከአውሮፓውያኑ 2001 እስከ 2005 የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤትን በበላይነት የመሩት ኮሊን ፖውል የህልፈታቸው መንስኤ የኮሮና ቫይረስ መሆኑን ቤተሰቦቻቸው ገልጸዋል ነው የተባለው።
ኮሊን ፖውል ሲቪል ባለስልጣን ከመሆንም ባለፈ ወታደራዊ ኃላፊነት እንደነበራቸው ተገልጿል። የቀድሞው ሚኒስትር ቤተሰቦች እንዳሉት ኮሊን ፖውል ሙሉ በሙሉ ተከትበው ነበር።
ለዚህም የቀድሞው ሚኒስትር ቤተሰቦች የዋልተር ሬድ ብሔራዊ የሕክምና ማዕከል ላደረገላቸው የህክምና አገልግሎት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ኮሊን ፖውል በፕሬዝዳንት ሮናልድ ሬገን የአስተዳደር ዘመን ብሔራዊ የደህንነት አማካሪ በመሆን ማገልገላቸው ተገልጿል፡፡ ኮሊን ፖውል በአውሮፓውያኑ 2001 በፕሬዝዳንት ቡሽ ዘመን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሆናቸው ይታወሳል፡፡
የቀድሞው ሚኒስትር በወቅቱ ኃላፊነቱን ሲረከቡ መስሪያ ቤትን የመሩ የመጀመሪያው ጥቁር አሜሪካዊ ነበሩ፡፡ ከቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኋላ በአሜሪካ ከፍተኛ ኃላፊነት ላይ የነበሩት የቀድሞዋ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኮንዶሊዛ ራይዝ እና ቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ናቸው፡፡
የአሁኑ የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትር Lloyd Austin ም ጥቁር አሜሪካዊ ናቸው።