በስፔንም በርካታ ተሳታፊዎች እና ጎብኝዎች ያሉት የቲማቲም ድብድብ ፌስቲቫል አለ
ኮሎምቢያ ከኮሮና ወረርሽኝ ወዲህ ግዙፉን የቲማቲማ ፌስቲቫል (ላ ቶማቲኖ) አስተናግዳለች።
ከመዲናዋ ቦጎታ በስተሰሜን የምትገኘው ሱታማርቻን ከተማም ነጭ ቲሸርት በለበሱ የፌስቲቫሉ ተሳታፊዎች ደምቃለች።
ከረጃጅም ተሽከርካሪዎች የተራገፈውን ቲማቲም አንዱ ባንዱ ላይ እየወረወረም የምርት ዘመኑ መጠናቀቅን አብስረዋል።
በኮሎምቢያ በየአመቱ የሚካሄደው የቲማቲም ፊስቲቫል ረጅም ዘመን ማስቆጠሩ የሚነገር ሲሆን፥ በውድድሩ ላይ ጥቅም ላይ የሚውለው ቲማቲም በጣም የበሰለና ለምግብነት የማይውል መሆኑ ተገልጿል።
በስፔንም በርካታ ተሳታፊዎች እና ጎብኝዎች ያሉት የቲማቲም ድብድብ ፌስቲቫል አለ።
የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ትዊተር: https://twitter.com/AlAinAmharic