በ200 ሜትር ከፍታ እስከ 15 ደቂቃዎች መብረር መቻሏ በሙከራው ተረጋግጧል
ቻይና “ዩፎ” መሰሏን በራሪ ተሸከርካሪ ሞከረች።
በ”ሸንዘን ዩፎ ፖወር ቴክኖሎጂ” የተሰራችው በራሪ ተሽከርካሪ አብራሪና የተወሰኑ ሰዎችን ታሳፍራለች ተብሏል።
ከየብስም ሆነ ከውሃ ላይ መነሳት የምትችል ሲሆን፥ የሙከራ በረራዋን በሸንዘን ከተማ አድርጋለች።
ክብ ቅርጽ ያላት በራሪን ለመስራት ሶስት አመት መውሰዱ የተነገረ ሲሆን፥ ለአጫጭር ጉዞና ለጉብኝት እንደምትወል ተገልጿል።
በሰው ልጅ የተሰራችው “ዩፎ” በ200 ሜትር ከፍታ እስከ 15 ደቂቃዎች መብረር መቻሏ በሙከራው ተረጋግጧል።
የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ትዊተር: https://twitter.com/AlAinAmharic