ፖለቲካ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከ1.17 ትሪሊዮን ብር መሻገሩን አስታወቀ
ባንኩ በበጀት ዓመቱ 135.4 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ማግኘቱን አስታውቋል
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደንበኞቹ ቁጥር ከ45 ሚሊዮን በላይ ሆኗል
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በበጀት ዓመቱ 135.4 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ማግኘቱን በመግለጽ፤ ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ13% ዕድገት አሳይቷል ብሏል።
ባንኩ በ2023/24 ወይም የ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸሙን በማበራዊ ትስስር ገጹ ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ በበጀት ዓመቱ ስኬት ማስመዝገቡንም አስታውቋል።
ባንኩ በበጀት ዓመቱ ከታክስ በፊት 25.6 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱንም ያስታወቀ ሲሆን፤ ይህም በባንኩ ታሪክ ከፍተኛው ሆኖ መመዝገቡንም ነው ባንኩ የገለጸው።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከ1.17 ትሪሊዮን ብር መሻሩን ያስታወቀ ሲሆን፤ የባኩ ደንበኞች ቁጥር ደግሞ ከ45 ሚሊዮን በላይ ደርሷል ነው ያለው በመግለጫው።
በበጀት ዓመቱ በቁጥር ከ1.56 ቢሊዮን የሚበልጥ ግብይት፤ ወይም በገንዘብ ከብር 31.6 ትሪሊዮን በላይ የገንዘብ ዝውውር በፈጸሙንም ባኩ አስታውቋል።