ንግድ ባንክ “የወሰዱትን ግንዘብ ለመመለስ ፍቃደኛ አልሆኑም” ያላቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር ይፋ አደረገ
ባንኩ ስመ ዝርዝራቸው የወጣ ሰዎች እስከ ቅዳሜ መጋቢት 21 ድረስ ገንዘቡን እንዲመልሱ አሳስቧል
እስካሁን 14 ሺህ 441 ሰዎች ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ እና በከፊል መልሰዋል ተብሏል
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባሳለፍነው ሳምንት መጋቢት 6 2016 ዓ.ም የተፈጠረውን የሲስተም ችግር ተከትሎ ያለ አግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱት ሰዎችን ስም ዝርዝር ይፋ አደረገ።
ባንኩ ዛሬ ማምሻውን በድረ ገጹ እና በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ገንዘብ አልመለሱም ያላቸውን የ565 ሰዎች ስም ዝርዝር ከነ ሂሳብ ቁጥራቸው እና የባንክ ቅርንጫፋቸው ይፋ አድርጓል።
ባንኩ ያወጣውን ስም ዝርዝር እዚህ ተጭነው ይመልከቱ
ስማቸው የተዘረዘረው 565 ግለሰቦች ባንኩ የሰጠውን ዕድል በመጠቀም ያላግባብ የወሰዱትን ገንዘብ እስከ ቅዳሜ መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ድረስ ገንዘቡን እንዲመልሱም አሳስቧል።
ባንኩ ከዚህ ቀደም በሰጠው እድል ተጠቅመው በዚህ መሰረት 14441 የሚሆኑ ግለሰቦች በተሰጠው ጊዜ ገደብ ተጠቅመው የወሰዱትን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ እና በከፊል መመለሳቸውንም አስታውቋል።
በዚህም ባንኩ ሊሰረቅ ከነበረ 801.4 ሚሊየን ብር ውስጥ እስካሁን 623 ሚሊየኑን ማለትም 78 በመቶውን ማስመለስ መቻሉን ገልጿል።
ስም ዝርዝራቸው ይፋ የተደረጉ 565 የባንኩ ደንበኞች የወሰዱት የገንዘብ መጠንም 9.8 ሚሊየን ብር መሆኑን ባንኩ አስታውቋል።
ባንኩ ያወጣውን ስም ዝርዝር እዚህ ተጭነው ይመልከቱ