በቲክቶክ አማካኝነት የተፈጠሩ አዳዲስ ቃላቶችና ምህጻረ ቃሎች ትርጉም ምንድን ነው?
በቲክቶክ አማካኝነት ለበርካቶች ግራ የሚያጋቡ አዳዲስ ቃላቶችና ምህፃረ ቃላት ተፈጥረዋል
በቲክቶክ ላይ ከተፈጠሩ አዳዲስ ምህጻረ ቃላትና ቃላቶች መካከል “FYP፣ CEO፣ OOMF እና Sheesh” ተጠቃሽ ናቻው
የአጫጭር ቪዲዮ ማጋሪያ የሆነው ቲክቶክ መምጣቱን ተከትሎ በተጠቃሚዎች ዘንድ አዳዲስ ቃላቶችና ምህጻረ ቃሎች ተፈጥረው ጥቅም ላይ በመዋል ላይ ይገኛሉ።
አንዳንዶቹ ቃላቶችና ምህጻረ ቃላት አዘውትረው ቲክቶክን ለሚጠቀሙ ሰዎች ካልሆነ በስተቀር ለሌሎች ተጠቃሚዎም ግራ የሚያጋቡ እና ትርጉማቸው የማይገባ ሆነው ሰዎች ለመረዳት ሲቸገሩ ይስተዋላል።
በቲክቶክ አማካኝነት የተፈጠሩ አዳዲስ ቃላቶችና ምህጻረ ቃሎች ከእና ትርጉማቸው እንደሚከተለው ቀርበዋል።
ሲ.ኢ.ኦ (CEO) የቲክቶክ ትርጉሙ ምንድን ነው?
በመደበኛው የዋና ስራ አስፈጻ ምህጻረ ቃል የያዘው “CEO” በቲክቶክ ላይ ግን የተለየ ትርጉም አለው የተባለ ሲሆን፤ ይህ ምህጻረ ቃል በቲቶክ ለይ አንድ ሰው በሆነ ነገር ላይ የተካነ ወይም ልዩ ችሎታ ያለው መሆኑን ለማመላከት ነው ጥቅም ላይ የሚውለው።
ለምሳሌ አንድን ሰው የዳስ ተሰጥኦ ለማድነቅ እሱ ወይም እሷ የዳንስ ሲ.ኢ.ኦ (CEO) ነው ወይም ነች በሚለው ጥቅም ላይ ይውላል።
ኤፍ.ዋይ.ፒ (FYP) የቲክቶክ ትርጉሙ ምንድን ነው?
FYP (For You Page) የሚለውን ምህጻረ ቃል የሚወክል ሲሆን፤ ትርጉሙም ለአንት/አንቺ ገጽ የሚለውን ያመላክታል።
በዚህ ምህጻረ ቃልም ተጠቃሚዎች በቲክቶክ ላይ የቪዲዮ ይዘት ከለቀቁ በኋላ በቲክቶክ ቀመር (አልጎሪዝም) መሰረት በርካታ ተጠቃሚ ለማግኘት በሃሽታግ መልክ የሚጠቀሙበት ምህጻረ ቃል ነው።
ለምሳሌ አንድ ቪዲዮ ከተለቀቀ በኋላ በቪዲዮው ማብራሪያ ላይ #FYP በሚል በማስገባት በርካታ ተመልካች ለመሳብ ይጠቅማል።
ኦ.ኦ.ኤም.ኤፍ (OOMF) በቲክቶክ ትርጉሙ ምንን ይወክላል?
OOMF (One of My Followers) የሚለውን ምህጻረ ቃል የሚወክል ሲሆን፤ ትርጉሙም ከተከታዮቼ አንዱ የሚለውን ለመግለጽ ጥቅም ላይ የሚውል ነው።
ይህም ተጠቃሚዎች ስም ሳይጠቅሱ ስለ ተከታያቸው ማውራት ሲፈልጉ የሚጠቀሙበት ምህጻረ ቃል።
“4Lifers” በቲክቶክ ትርጉሙ ምንን ይወክላል?
በቲክቶክ አማካኝነት የተሰባሰበዉ እና ጓደኝነት የፈጠሩ ሰዎች “4Lifers” የሚል መጠሪያ ያላቸው ሲሆን፤ እነዚህ ሰዎች አርስ በእርስ የሚደጋገፉ እና አንዳቸው በአንዳቸው ይዘት ላይ ለረጅም ጊዜ ተሳትፎ የሚያደርጉ ሰዎች ናው።
ቼውጊይ (Cheugy) በቲክቶክ ትርጉሙ ምንን ይወክላል?
ቼውጊይ በቲክቶክ ላይ ከተፈጠሩ ቃላቶች አንዱ ሲሆን፤ ትርጉሙም በአንድ ወቅት በጣም መነጋገሪያ ወይም ትሬንድ የነበረ እና አሁን ላይ እምብዛም ተመልካች የማያገኝ ነገርን ለመገልጽ ጥቅም ላይ የሚውል ነው።
“#xyzbca” በቲክቶክ ትርጉሙ ምንን ይወክላል?
“#xyzbca” የሚለው ሃሽታግ ብዙ ጊዜ በአስተያየት መስጫ ላይ ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን ይህም የቲክቶክ አልጎሪዝም የቪድዮውን መጨረሻ እንዲለይ እና በርካታ ተመልካች ለመሳብ ጥቅም ላይ የሚውል ነው።
ተጠቃሚዎች የቪዲዮቸውን እይታ ለማሳደግ ተስፋ በማድረግ በዚህ ተከታታይ ፊደሎች አስተያየት መስ ላይ ያስቀምጣሉ ።
ለምሳሌ፤ Great dance routine! #xyzbca በሚል ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።
“Sheesh” የቲክቶክ ትርጉሙ ምንድን ነው?
የቲክቶቶክ ተጠቃሚዎች አንድ ቪዲዮ ላይ ያላቸውን መገረም፣ አድናቆት እንዲሁም ሰርፕራይዝ ለመግለጽ “Sheesh” የሚለውን ቃል በብዛት ሲጠቀሙ ይስተዋላል።
ለምሳሌ፤ በጣም የሚያስገርም ስራ ነው የሰራኸው! Sheesh! በዚህ መልኩ ጥቅም ላይ መዋል ይችላል።