ኮመንዌልዝ ድርድት ለአየር ንብረት ፋይናንስ 320 ሚሊዮን ዶላር ሰበሰበ
በአረብ ኢምሬትስ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ያለው ኮፕ28 ወይም የተመድ የአየር ንብር ስብሰባ ዛሬ ይጠናቀቃል
ኃላፊው እንደናገሩት ዝቅተኛ የካርበን ልቀት እንዲኖር እና የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስክለውን ችግር ለመቀነስ ፋይናነስ አስፈላጊ ነው
ኮመንዌልዝ ድርድት ለአየር ንብረት ፋይናንስ 320 ሚሊዮን ዶላር ሰብስቧል።
የኮመንዌልዝ ድርጅት ለዝግጁት ከተመደበው 500 ሚሊዮን ዶላር በተጨማሪ 320 ሚሊዮን ዶላር መሰብሰቡን አስታውቋል።
በድርጅቱ የአየር ንብረት ለውጥ ዲፖርትመንት ኃላፊ ኒክርሻን ዲቫከራን የአየር ንብረት ፋይናንስ በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ኢንቨስት ለማድረግ ወሳኝ ነው ብለዋል።
ኃላፊው እንደናገሩት ዝቅተኛ የካርበን ልቀት እንዲኖር እና የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስክለውን ችግር ለመቀነስ ፋይናነስ አስፈላጊ ነው።
የኮመንዌልዝ ባለስልጣናት ከኮፕ28 ስብሰባ ጎንለጎን ለአረብ ኢምሬትስ ዜና አገሌግሎት እንደተናገሩት ይህ ስብሰባ ሰዎች በበርካታ ዘርፍ አብረው እንዲሰሩ እና የአየር ንብረት ፕሮጀክቶችን ለመፈጸም በባለድርሻ አካላት መካከል መነጋገር እንዲኖር እድል ፈጥሯል።
ዲቫክራን የኮመንዌልዝ ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ፈንድ ያቋቋመው በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን ለመርዳት እና የድርጅቱን የአየር ንብረት ለውጥ የመዋጋት ቁርጠኝነት ለመጨመር መሆኑን ገልጸዋል።
በአረብ ኢምሬትስ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ያለው ኮፕ28 ወይም የተመድ የአየር ንብር ስብሰባ ዛሬ ይጠናቀቃል።