ተመድ 180 ሚሊዮን ገደማ ህዝብ ለመርዳት የሚውል ፈንድ ለመሰብሰብ ማቀዱን ገለጸ
አለምቀፍ ተቋማት ለእርዳታ የሚውል በቂ ፈንድ አለማግኘት ከፍተኛ ቀውስ ያስከትላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
2023 ከ2010 ወዲህ አለምአቀፍ እርዳታ የቀነሰበት አመት መሆኑ ተገልጿል
ተመድ 180 ሚሊዮን ገደማ ህዝብ ለመርዳት የሚውል ፈንድ ለመሰብሰብ ማቀዱን ገለጸ
ተመድ በ2024 በግጭት፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና በኢኮኖሚ ቀውስ ምክንያት የተጎዳ 180 ሚሊዮን ህዝብ ለመርዳት የ46.4 ቢሊዮን ዶላር ለመሰብሰብ አቅዷል።
አለምቀፍ ተቋማት ለእርዳታ የሚውል በቂ ፈንድ አለማግኘት ከፍተኛ ቀውስ ያስከትላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ትኩረት የተደረገው በእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት ላይ ቢሆንም፣ ተመድ ባወጣው መግለጫ ግን እንደ ሱዳን እና አፍጋኒስታን ያሉ ሀገራት ወሳኝ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ብሏል።
"የሰብአዊ ሰራተኞች ህይወት ያድናሉ፣ ረሃብን ይዋጋሉ፣ ህጻናትን ይጠብቃሉ፣ከወረርሽኝ ይከላከላሉ" ያሉት የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊትስ ነገርግን አለምአቀፍ ማህብረሰብ በቂ ድጋፍ እያቀረበ አለመሆኑን ተናግረዋል።
ተመድ በ2023፣ 56.7 ቢሊዮን ዶላር ለመሰብሰብ አቅዶ የነበረ ቢሆንም መሰብሰብ የተቻቸው 35 በመቶውን ብቻ ነው።
የተመድ ኤጀንሲዎች 128 ሚሊዮን ለሚሆን ህዝብ ድጋፍ እና ጥበቃ ያደርጋል።
2023 ከ2010 ወዲህ አለምአቀፍ እርዳታ የቀነሰበት አመት መሆኑ ተገልጿል።
ተመድ ለ2024 ያቀረበውን የገንዘብ ጥያቄ ዝቅ በማድረግ አስቸኳይ ድጋፍ በሚያስፈልጋቸው ላይ ትኩረት አድርጓል።
ተመድ ድጋፉን ከ72 ሀገራት ለመሰብሰብ አቅዷል።