የሶስቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለአውሮፖ ህብረት በጻፉት ደብዳቤ በሀማስ ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ጠይቀዋል
ሶስት የአውሮፖ ሀገራት በሀማስ ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ጠየቁ።
ጣሊያን፣ ፈረንሳይ እና ጀርመን የአውሮፖ ህብረት በሀማስ እና በደጋፊዎቹ ላይ ማዕቀብ እንዲጥል ጥሪ አቅርበዋል።
የሶስቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለአውሮፖ ህብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊ ጆሴፍ ቦሬል በጻፉት ደብዳቤ በሀማስ ላይ ማዕቀብ እንዲጣል መጠየቃቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ሚኒስትሮቹ እንደገለጹት በሀማስ እና በደጋፊዎቹ ላይ የሚጣል ማዕቀብን ይደግፋሉ።
ሚኒስትሮቹ "የዚህ ማዕቀብ በፍጥነት ተግባራዊ መሆን ህብረቱ በሀማስ ላይ ያለውን አቋም እና ለእስራኤል ስላለን አጋርነት ጠንካራ መልእክት እንድናስተላልፍ ያስችለናል" ብለዋል።
በኳታር አደራዳሪነት የተደረሰው ተኩስ አቁም ከተጣሰ በኋላ እስራኤል በጋዛ ጠንካራ የእግረኛ ጦር እና የአየር ድብደባ እያካሄደች ትገኛለች።
በጋዛ ተኩስ እንዲቆም አለምአቀፍ ጫና ቢደረግም እስራኤል ተኩስ ለማቆም ፍቃደኛ አልሆነችም።
የተመድ የጸጥታው ምክርቤት በጋዛ ተኩስ እንዲቆም ያቀረበው የውሳኔ ሀሳብ አሜሪካ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብቷን ተጠቅማ እንዳይጸድቅ አድርጋዋለች።
እስራኤል እና አጋሯ አሜሪካ የተኩስ አቁሙን ሀሳብ የማይቀበሉት የሚጠቀም ሀማስ ብቻ ነው በሚል ምክንያት ነው።
ጦርነቱ ከተቀሰቀሰበት ከባለፈው ጥቅምት ወዲህ በጋዛ 18ሺ ገደማ ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የፍልስጤም ባለስልጣናት ገልጸዋል።
ሀማስን ከምድገጽ አጠፋለሁ የምትለው እስራኤልም ጥቃቷን አጠናክራ ቀጥላለች።