አረብ ኢምሬትስ ፍትሃዊ ስምምነቶች እንዲደረሱ ጥረት ማድረጓን ገለጸች
ዶክተር ጃብር ይህን የናገሩት የኮፕ28 ስብሰባን እየተካፈሉ ላሉ በርካታ ሚኒስትሮች እና የልኡክ ቡድን መሪዎች ነው
ዶክተር ጃብር "መጨረሻው ደረጃ ላይ ደርሰናል፣ አለም በዘላቂ ልማት እና በአየር ንብረት ለውጥ ቅነሳ መካከል ሚዛን እንዲጠበቅ ይፈልጋል። ብለዋል
አረብ ኢምሬትስ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቀንሱ ፍትሃዊ ስምምነቶች እንዲደረሱ ጥረት ማድረጓን ገለጸች።
የኮፕ28 ፕሬዝደንት አረብ ኢምሬትስ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ የሚረዱ ፍትሃዊ ስምምነቶች እንዲደረሱ ሁሉንም አይነት ጥረት ማድረጓን ገልጸዋል።
የኮፕ28 ስብሰባ ፕሬዝደንት ዶክተር ሱልጣን አል ጃብር አረብ ኢምሬትስ የአየር ንብረት ለውጥ ለመቀነስ የሚያስችሉ ድርድሮች ፍትሃዊ ስምምነት ላይ እንዲደርሱ አስፈላጊውን ጥረት ማድረጓን ተናግረዋል።
ዶክተር ጃብር ይህን የተናገሩት የኮፕ28 ስብሰባን እየተካፈሉ ላሉ በርካታ ሚኒስትሮች እና የልኡክ ቡድን መሪዎች ነው።
ፕሬዝደንቱ የስብሰባው ተሳታፊዎች በቁርጠኝነት ወደ ተግባር እንዲገቡ ጥሪ አቅርበዋል
ዶክተር ጃብር "መጨረሻው ደረጃ ላይ ደርሰናል፣ አለም በዘላቂ ልማት እና በአየር ንብረት ለውጥ ቅነሳ መካከል ሚዛን እንዲጠበቅ ይፈልጋል። ብለዋል።
መሻሻሎች መታየታቸውን የገለጹት ዶክተር ጃብር ነገርግን አሁንም በፍጥነት መንቀሳቀስ ላይ ችግር መኖሩን ተናግረዋል።
በአረብ ኢምሬትስ አስተናጋጅነት እየተካሄደ የኮፕ28 ወይም የተመድ የአየር ንብረት ጉባኤ 198 ሀገራት ተሳትፈውበታል
ስብሰባው ዛሬ 12ኛ ቀኑን አስቆጥሯል።