የኮሞሮስ ፕሬዝዳንት ለልጃቸው ያልተገባ ስልጣን መስጠታቸው ተገለጸ
ፕሬዝዳንት አዛሊ አሱማኒ ለልጃቸው ስልጣን ማስተላለፍ የሚያስችል ህግ አጽድቀዋል ተብሏል
800 ሺህ ህዝብ ያላት ኮሞሮስ ከ20 በላይ መፈንቅለ መንግሥት ተፈጽሞባታል
የኮሞሮስ ፕሬዝዳንት ለልጃቸው ያልተገባ ስልጣን መስጠታቸው ተገለጸ።
ደቡብ አፍሪካዊቷ ሀገር ኮሞሮስ ፕሬዝዳንት የሆኑት አዛሊ አሱማኒ ስልጣን ለልጃቸው እንዲያስተላልፉ የሚያግዝ ህግ አጽድቀዋል።
አዲሱ ህግ ከአንድ ወር በፊት የጸደቀ ሲሆን ተቃዋሚዎች እና አንቂዎች ትችቶችን እየሰነዘሩ ናቸው።
የ65 ዓመቱ ፕሬዝዳንት አሱማኒ እስከ 2029 ድረስ የኮሞሮስ ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲቀጥሉ ባሳለፍነው ጥር ወር ላይ የተካሄደውን ምርጫ አሸንፈዋል።
ፕሬዝዳንቱ የ40 ዓመት ልጃቸው ስልጣን እንዲይዝ ያደረጉ ሲሆን ቀስ በቀስም የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ መንገድ ለመጥረግ ያለመ ህግ አጽድቀዋል የሚል ትችቶች ቀርቦባቸዋል።
እንደ ሮይተርስ ዘገባ የፕሬዝዳንቱ ወንድ ልጅ ኤል ፋዝ አዲስ ስልጣን የተሰጣቸው ሲሆን የሀገሪቱን ሁሉንም ተቋማት እና አመራሮች እንዲገመግሙ ይፈቅድላቸዋል።
የኮሞሮስ መንግሥት ቃል አቀባይ ፋቲማ ሀማዳ በበኩላቸው የፕሬዝዳንቱ አዲስ ህግ ሀላፊነቶችን ለተቋማት ያከፋፈለ እንጂ ስልጣን ለፕሬዝዳንቱ ልጅ የሰጠ አይደለም ብለዋል።
800 ሺህ ህዝብ ብዛት ያላት ኮሞሮስ የፈረንሳይ የቀድሞ ቅኝ ተገዢ ሀገር ነበረች።
የወቅቱ ፕሬዝዳንት አዛሊ አሱማኒ በ1975 ከቅኝ ግዛት ነጻ የወጣችው ኮሞሮስን ከ1999 ጀምሮ እይመሩ ይገኛሉ።
በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን የተቆጣጠሩት ፕሬዝዳንቱ ከ2002 ጀምሮ ደግሞ ምርጫ እያካሄዱ ስልጣን ይዘው እንደቀጠሉ ናቸው።